Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 47:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ በዳሩ ላይ በዚ​ህና በዚያ ፍሬው የሚ​በላ ዛፍ ሁሉ ይበ​ቅ​ላል፤ ቅጠ​ሉም አይ​ረ​ግ​ፍም፤ ፍሬ​ውም አይ​ጐ​ድ​ልም፤ ውኃ​ውም ከመ​ቅ​ደስ ይወ​ጣ​ልና በየ​ወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገ​ኛል፤ ፍሬ​ውም ለመ​ብል፥ ቅጠ​ሉም ለመ​ድ​ኀ​ኒት ይሆ​ናል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በወንዙም ዳርና ዳር፣ ፍሬ የሚያፈሩ የዛፍ ዐይነቶች ሁሉ ይበቅላሉ፤ ቅጠላቸው አይደርቅም፤ ፍሬ አልባም አይሆኑም። ከመቅደሱ የሚወጣው ውሃ ስለሚፈስላቸው በየወሩ ያፈራሉ፤ ፍሬአቸው ለምግብ፣ ቅጠላቸውም ለፈውስ ይሆናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉ አይረግፍም ፍሬውም አያልቅም፤ ውኃው ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኩር ያፈራል፤ ፍሬው ለመብል ቅጠሉም ለፈውስ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በፈሳሹ ውሃ ዳርና ዳር ለምግብ የሚሆኑ ተክሎች በየዐይነቱ ይገኛሉ፤ እነርሱም ቅጠሎቻቸው አይደርቁም፤ ፍሬ ማፍራትንም አያቋርጡም፤ ከቤተ መቅደሱ ሥር የሚፈሰውን ወንዝ ውሃ ስለሚያገኙ በየወሩ አዲስ ፍሬ ያፈራሉ፤ ዛፎቹ ፍሬአቸው ለምግብ፥ ቅጠላቸው ለፈውስ የሚጠቅም ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይጐድልም፥ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፥ ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 47:12
11 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ።


ከፀ​ሐይ በታች ይሻ​ግ​ታል፤ ጫፉም በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ይወ​ጣል።


እር​ሱም በውኃ ፈሳ​ሾች ዳር እንደ ተተ​ከ​ለች፥ ፍሬ​ዋን በየ​ጊ​ዜዋ እን​ደ​ም​ት​ሰጥ፥ ቅጠ​ል​ዋም እን​ደ​ማ​ይ​ረ​ግፍ ዛፍ ይሆ​ናል፤ የሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ለ​ታል።


ከእ​ግር ጫማ አን​ሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለ​ውም፤ ቍስ​ልና እበጥ የሚ​መ​ግ​ልም ነው፤ አል​ፈ​ረ​ጠም፤ አል​ተ​ጠ​ገ​ነ​ምም፤ በዘ​ይ​ትም አል​ለ​ዘ​በም።


ሕዝ​ብሽ ሁሉ ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ፤ ምድ​ር​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሳሉ፤ እር​ሱ​ንም ለማ​መ​ስ​ገን የእ​ጆ​ቹን ሥራ ይጠ​ብ​ቃሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።


በውኃ አጠ​ገብ እንደ ተተ​ከለ፥ በወ​ን​ዝም ዳር ሥሩን እን​ደ​ሚ​ዘ​ረጋ፥ ሙቀ​ትም ሲመጣ እን​ደ​ማ​ይ​ፈራ፥ ቅጠ​ሉም እን​ደ​ሚ​ለ​መ​ልም፥ በድ​ርቅ ዓመ​ትም እን​ደ​ማ​ይ​ሠጋ ፍሬ​ው​ንም እን​ደ​ማ​ያ​ቋ​ርጥ ዛፍ ይሆ​ናል።


በገ​ለ​ዓድ መድ​ኀ​ኒት የለ​ምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለ​ምን? የወ​ገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አል​ሆ​ነም?


በተ​መ​ለ​ስ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በወ​ንዙ ዳር በዚ​ህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።


በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告