Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት በስ​ድ​ስቱ ቀን ተዘ​ግቶ ይቈይ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት ቀን ይከ​ፈት፤ በመ​ባቻ ቀንም ይከ​ፈት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ለምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው አደባባይ በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በወር መባቻ ቀን ይከፈት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት እንዲሁም በወር መባቻ ቀን ይከፈት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚያመለክተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ዝግ መሆን አለበት፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በየወሩ መባቻ ቀን ይከፈታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ፥ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በመባቻ ቀን ይከፈት።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:1
15 交叉引用  

ወደ ወጣ​ህ​በት መሬት እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ በፊ​ትህ ወዝ እን​ጀ​ራ​ህን ትበ​ላ​ለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈ​ርም ትመ​ለ​ሳ​ለ​ህና።”


እስ​ከ​ዛ​ሬም ድረስ በን​ጉሥ በር በም​ሥ​ራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረ​ኞች ነበሩ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ተግ​ባ​ር​ህ​ንም ሁሉ አድ​ርግ፤


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፦ በየ​መ​ባ​ቻ​ውና በየ​ሰ​ን​በቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በፊቴ ይሰ​ግድ ዘንድ ዘወ​ትር ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰው​የ​ውም ሲገባ ኪሩ​ቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፤ ደመ​ና​ውም ውስ​ጠ​ኛ​ውን አደ​ባ​ባይ ሞላ።


ከታ​ች​ኛ​ውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ፊት ድረስ ወር​ዱን አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ሰሜን ለካ።


ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አመ​ጣኝ።


አለ​ቃ​ውም በፈ​ቃዱ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በፈ​ቃዱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ይከ​ፈ​ት​ለት፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ ከወ​ጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።


የሀ​ገ​ርም ሕዝብ በዚያ በር መግ​ቢያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሰ​ን​በ​ታ​ትና በመ​ባቻ ይስ​ገዱ።


በመ​ባ​ቻም ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አንድ ወይ​ፈን፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ው​ንም ስድ​ስት ጠቦ​ቶ​ችና አንድ አውራ በግ ያቅ​ርብ፤


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


የም​ኵ​ራቡ ሹምም ጌታ ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ፈው​ሶ​አ​ልና፤ እየ​ተ​ቈጣ መልሶ ሕዝ​ቡን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሥራ​ች​ሁን የም​ት​ሠ​ሩ​ባ​ቸው ስድ​ስት ቀኖች ያሉ አይ​ደ​ለ​ምን? ያን​ጊዜ ኑና ተፈ​ወሱ፤ በሰ​ን​በት ቀን ግን አይ​ሆ​ንም።”


跟着我们:

广告


广告