ሕዝቅኤል 45:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ይህም በእስራኤል ዘንድ ይዞታ ይሆንለታል፤ የሕዝቤ አለቆችም ለእስራኤል ቤት ምድሪቱን እንደ ነገዳቸው መጠን ይሰጡአቸዋል እንጂ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ይህም መሬት በእስራኤል ምድር የገዢው ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ ገዥዎቼ ሕዝቤን አይጨቍኑም፤ ነገር ግን የእስራኤል ቤት በየነገዳቸው ርስት እንዲይዙ ይፈቅዱላቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ይህም ከምድሪቱ በእስራኤል ዘንድ ርስት ይሆንለታል፥ መሪዎቼ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም፥ ነገር ግን ምድሪቱን ለእስራኤል ቤት እንደ ነገዳቸው ይሰጡአቸዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ይህም ክልል በእስራኤል ምድር መሪ ለሚሆነው መስፍን የርስት ድርሻ ይሆናል፤ ከዚህም በኋላ መሪዎች ሁሉ ሕዝቡን መጨቈን የለባቸውም፤ ነገር ግን ከሀገሪቱ ቀሪውን ምድር በሙሉ ለእስራኤል ነገዶች መተው ይኖርባቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ይህም በእስራኤል ዘንድ ይዞታ ይሆንለታል፥ አለቆቼም ለእስራኤል ቤት ምድሪቱን እንደ ነገዳቸው መጠን ይሰጡአቸዋል እንጂ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም። 参见章节 |