Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 45:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለአ​ለ​ቃ​ውም የሆነ የዕጣ ክፍል በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ አጠ​ገብ በዚ​ህና በዚያ ይሆ​ናል፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ ፊት በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ምዕ​ራብ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወደ ምሥ​ራቅ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከም​ድሩ ከም​ዕ​ራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘ገዥው ከቅዱሱ ስፍራና ከከተማው ወሰን ግራና ቀኝ ርስት ይኖረዋል፤ ይህም ከምዕራብ በኩል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ምሥራቅ በመዝለቅ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያለውን ወሰን ርዝመት ተከትሎ ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ርስት ጋራ ጐን ለጐን ይሄዳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለአለቃውም የሚሆነው የዕጣ ክፍል በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ አጠገብ በጎንና በጎን ይሆናል፤ በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ ፊት በምዕራብ በኩል ወደ ምዕራብ በምሥራቅም በኩል ወደ ምሥራቅ ይሆናል፤ ርዝመቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከምድሩ ከምዕራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የሀገሪቱም መሪ ድርሻ ከተቀደሰው ቦታና ከከተማው ክልል ቀጥሎ በሁለቱም በኩል ማለትም በስተምዕራብ እስከ ሀገሪቱ ድንበር ሲደርስ በስተ ምሥራቅም እስከ ሀገሪቱ ድንበር የሚደርስ ይከለላል፤ ርዝመቱም ለአንድ ነገድ የሚደርሰውን ድርሻ ያኽላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ለአለቃውም የሆነ የዕጣ ክፍል በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ አጠገብ በዚህና በዚያ ይሆናል፥ በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ ፊት በምዕራብ በኩል ወደ ምዕራብ በምሥራቅም በኩል ወደ ምሥራቅ ይሆናል፥ ርዝመቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከምድሩ ከምዕራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 45:7
8 交叉引用  

እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ባሪ​ያዬ ዳዊ​ትም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።


“በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ፥ በዚ​ህና በዚያ ወገን የቀ​ረው ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ በመ​ባው በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምሥ​ራቁ ድን​በር፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምዕ​ራቡ ድን​በር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም መባና ቤተ መቅ​ደሱ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።


ምድ​ሩ​ንም ሁሉ በየ​ድ​ን​በሩ ርስት እን​ዲ​ሆን ከፍ​ለው ከጨ​ረሱ በኋላ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢ​ያሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ርስት ሰጡት።


跟着我们:

广告


广告