ሕዝቅኤል 45:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶው አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ ኀጢአታችሁን ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እንዲሁም ውሃ ከጠገበው ከእስራኤል መሰማሪያ፣ ሁለት መቶ በግ ካለው ከእያንዳንዱ መንጋ አንድ በግ ይውሰድ። ይህ ሁሉ ለሕዝቡ ማስተስረያ ለሚሆነው ለእህል ቍርባን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለኅብረት መሥዋዕት ይውላል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ውኃም ካለበት ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለት መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፤ ይህ እንዲያስተሰርይላችሁ እህል ቁርባን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሰላም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እንዲሁም ከእስራኤል የበግ መንጋዎች መካከል ከየሁለት መቶ በግ የተመደበው አንድ በግ ነው፤ ይህም ለእነርሱ የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ከእህል ቊርባን ጋር የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ ነው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ውኃም ካለበት ከእስራኤል ማሰማርያ ከመንጋው ከሁለቱ መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ፥ ይህ ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 参见章节 |