Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በሰ​ሜ​ኑም በር መን​ገድ በቤቱ ፊት አገ​ባኝ፤ እኔም አየሁ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መል​ቶት ነበር፤ እኔም በግ​ም​ባሬ ተደ​ፋሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ያ ሰው በሰሜኑ በር በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አመጣኝ፤ እኔም ተመለከትሁ፤ የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሞልቶት አየሁ፤ በግንባሬም ተደፋሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በሰሜኑ በር መንገድ ወደ ቤቱ ፊት ለፊት አገባኝ፤ እኔም አየሁ፥ እነሆ የጌታ ክብር የጌታን ቤት ሞልቶት ነበር፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚያም በኋላ ያ ሰው በሰሜኑ ቅጽር በር በኩል አድርጎ ወደ ቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወሰደኝ፤ በዚያም ሆኜ ስመለከት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በክብሩ ተሞልቶ አየሁ፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በሰሜኑም በር መንገድ በቤቱ ፊት አመጣኝ፥ እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:4
18 交叉引用  

አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦


እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።


በዝ​ናብ ቀን በደ​መና ውስጥ እንደ አለ ቀስተ ደመና አም​ሳያ፥ እን​ዲሁ በዙ​ሪ​ያው ያለ ፀዳል አም​ሳያ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። በአ​የ​ሁም ጊዜ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፋሁ። የሚ​ና​ገ​ር​ንም ድምፅ ሰማሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርም ከኪ​ሩ​ቤል ወጥቶ በቤቱ መድ​ረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደ​መ​ናው ተሞላ፤ አደ​ባ​ባ​ዩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ፀዳል ተሞላ።


እኔም ተነ​ሥቼ ወደ ሜዳው ሄድሁ፤ እነ​ሆም በኮ​ቦር ወንዝ እን​ዳ​የ​ሁት ክብር ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፤ በግ​ም​ባ​ሬም ተደ​ፋሁ።


ወደ ሰሜ​ንም መራኝ፤ እነ​ሆም በው​ጭው አደ​ባ​ባይ ያለ ወደ ሰሜን የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንና ወር​ዱ​ንም ለካ።


በሰ​ሜ​ንም ወደ አለው በር አመ​ጣኝ፤ እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን ለካው፤


በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው በር በስ​ተ​ው​ጭው፥ በመ​ወ​ጣ​ጫው ደረ​ጃ​ዎች አጠ​ገብ፥ በአ​ንዱ ወገን ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ፤ በሌ​ላ​ውም ወገን በበሩ ደጀ ሰላም በኩል ሁለት ገበ​ታ​ዎች ነበሩ።


ወደ ሰሜ​ንም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም፥ ሴቶች ለተ​ሙዝ እያ​ለ​ቀሱ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።


አሕዛብን ሁሉ አናውጣለሁ፥ በአሕዛብ ሁሉ የተመረጠውም ዕቃ ይመጣል፣ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፤ እንዲህም አለኝ “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ፤


跟着我们:

广告


广告