Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የበ​ኵ​ራቱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ከቍ​ር​ባ​ና​ች​ሁም ሁሉ የማ​ን​ሣት ቍር​ባን ሁሉ ለካ​ህ​ናት ይሆ​ናል፤ በቤ​ታ​ች​ሁም ውስጥ በረ​ከት ያድር ዘንድ የአ​ዝ​መ​ራ​ች​ሁን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከፍሬ በኵራት ምርጥ የሆነው ሁሉ እንዲሁም ከልዩ ስጦታዎቻችሁ የመጀመሪያው ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ ለቤተ ሰዎቻችሁ ሁሉ በረከት እንዲሆን ከምድር የምታገኙትን መብል በኵራት ለእነርሱ ስጧቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የበኩራቱ ሁሉ መጀመሪያ፥ ስጦታ ሁሉ፥ ስጦታዎቻችሁ ሁሉ፥ ለካህናት ይሆናል፤ በቤትህም ውስጥ በረከት እንዲያድር የሊጣችሁን በኵራት ለካህን ትሰጣላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የመከር መጀመሪያ የሆነውን ያማረውን በኲራትና ለእኔ የቀረበውን ስጦታ ሁሉ ካህናቱ ይውሰዱ፤ ሕዝቡም ሁልጊዜ እህል ሲፈጩ የዱቄቱን በኲራት ለካህናቱ መባ አድርገው ያበርክቱ፤ እኔም ይህንን ሁሉ የሚያደርጉትን ሕዝብ ቤታቸውን በበረከት እሞላዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፥ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:30
17 交叉引用  

ከሳ​ዶ​ቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ “ሕዝቡ መባ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማቅ​ረብ ከጀ​መረ ወዲህ በል​ተ​ናል፤ ጠጥ​ተ​ና​ልም፤ ጠግ​በ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን ባር​ኮ​አ​ልና ብዙ ተር​ፎ​አል፤ ከዚ​ህም ገና ብዙ ተረፈ” ብሎ ተና​ገረ።


ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ ለይ፤ ከመ​ን​ጋ​ህና ከከ​ብ​ት​ህም መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለ​ደው ተባት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


የአ​ው​ድ​ማ​ህ​ንና የወ​ይ​ን​ህ​ንም መጀ​መ​ሪያ ለማ​ቅ​ረብ አት​ዘ​ግይ፤ የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ በኵ​ራት ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጣ። ጠቦ​ትን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።


በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ርን ሁሉ በመ​ታሁ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በኵ​ርን ሁሉ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን፥ ለእኔ ለይ​ች​አ​ለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ።


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ አስ​ቀ​ድ​ሞም የተ​ሸ​ለ​ተ​ውን የበ​ግ​ህን ጠጕር ለእ​ርሱ ትሰ​ጣ​ለህ።


ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።


跟着我们:

广告


广告