Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውና ባል​ተ​ቀ​ደ​ሰው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ሕዝ​ቤን ያስ​ተ​ምሩ፤ ንጹ​ሕና ንጹሕ ባል​ሆ​ነው መካ​ከል ይለዩ ዘንድ ያሳ​ዩ​አ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምሩ፤ የረከሰውንና ያልረከሰውን እንዴት እንደሚለዩም ያሳዩአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሕዝቤን ቅዱስ በሆነውና በረከሰው መካከል እንዲለዩ ያስተምሩ፥ ንጹሕ በሆነውና ንጹሕ ባልሆነው መካከል እንዲለዩ ያሳዩአቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ካህናቱ ለሕዝቤ ቅዱስ የሆነውንና ያልሆነውን ንጹሕ የሆነውንና ርኩስ የሚባለውን ነገር እንዲለዩ ያስተምሩአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፥ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:23
15 交叉引用  

ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብት​መ​ለስ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ቴም ትቆ​ማ​ለህ፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም ከተ​ዋ​ረ​ደው ብት​ለይ እንደ አፌ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ርሱ ወደ አንተ ይመ​ለ​ሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነ​ርሱ አት​መ​ለ​ስም።


ካህ​ና​ቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም መካ​ከል ቅድ​ሳ​ቴን አረ​ከሱ፤ ከር​ኵ​ሰ​ትም አል​ራ​ቁም፤ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ መካ​ከል ያለ​ው​ንም ልዩ​ነት አላ​ወ​ቁም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከሰ​ን​በ​ታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ረከ​ስሁ።


በአ​ራ​ቱም ወገን ለካ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ያል​ተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ይለይ ዘንድ ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ ክንድ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙ​ሪ​ያው ነበረ።


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


በር​ኩ​ስና በን​ጹሕ መካ​ከል፥ የሕ​ይ​ወት ነፍስ ካላ​ቸ​ውም በም​ት​በ​ሉ​ትና በማ​ት​በ​ሉት መካ​ከል እን​ድ​ት​ለዩ ነው።”


ካህ​ኑም ደዌ​ውን አይቶ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


በሚ​ረ​ክ​ስና በሚ​ነጻ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ውቅ ይህ የለ​ምጽ ሕግ ነው።”


ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፣ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል።


ፍር​ድ​ህን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሕግ​ህ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ በማ​ዕ​ጠ​ን​ትህ ዕጣ​ንን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ህም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሁል​ጊዜ ያቀ​ር​ባሉ።


跟着我们:

广告


广告