Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ነገር ግን በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም በሮች በረ​ኞች ይሆ​ናሉ፤ በቤ​ቱም ውስጥ ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ይሠ​ዋሉ፤ ያገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ በፊ​ታ​ቸው ይቆ​ማሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የቤተ መቅደሱ በር ኀላፊ በመሆንና በርሱም ውስጥ በማገልገል፣ መቅደሴን ሊያገለግሉ ይችላሉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐርደው ስለ ሕዝቡ ሊሠዉ፣ በፊታቸው ሊቆሙና ሊያገለግሏቸው ይችላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች፥ በቤቱም በሮች ዘበኞች ይሆናሉ፥ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕትን ያርዳሉ፥ ሊያገለግሉአቸውም በፊታቸው ይቆማሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነርሱ በቤተ መቅደሱ በር ጠባቂነት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሰዎች የሚያቀርቡአቸውን መሥዋዕቶች በማረድ፥ እንዲሁም ሰዎችን በማገልገል እንዲሠሩ ይፈቅድላቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ነገር ግን በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች ይሆናሉ፥ በቤቱም በሮች በረኞች ይሆናሉ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፥ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን ያርዳሉ፥ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:11
13 交叉引用  

ነገር ግን ካህ​ናቱ ጥቂ​ቶች ነበ​ሩና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለመ​ግ​ፈፍ አይ​ች​ሉም ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን በቅን ልብ ከካ​ህ​ናት ይልቅ ይቀ​ደሱ ነበ​ርና ሥራው እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ካህ​ና​ቱም እስ​ኪ​ቀ​ደሱ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያን ያግ​ዙ​አ​ቸው ነበር።


በጉ​ባ​ኤ​ውም ያል​ነጹ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ስለ​ዚ​ህም ሌዋ​ው​ያን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሳ​ቸ​ውን ላላ​ነ​ጹት ሁሉ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ያር​ዱ​ላ​ቸው ነበር።


ሰው​ዬ​ውም፥ “ይህ ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው።


ነገር ግን ለአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ሁሉና በእ​ርሱ ውስጥ ለሚ​ደ​ረ​ገው ሁሉ የቤ​ቱን ሥር​ዐት ጠባ​ቂ​ዎች አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “እነ​ዚህ የቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች የሕ​ዝ​ቡን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​ባ​ቸው ስፍ​ራ​ዎች ናቸው” አለኝ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ለይቶ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እን​ድ​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም በማ​ኅ​በሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁን ታሳ​ን​ሱ​ታ​ላ​ች​ሁን?


ደግ​ሞም የአ​ባ​ት​ህን የሌ​ዊን ነገድ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ወደ አንተ ሰብ​ስብ፤ ከአ​ን​ተም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​ህም፤ አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


እኔም፦ እነሆ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያደ​ርጉ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጡ ስጦ​ታ​ዎች ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


ወን​ድ​ሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ል​ግል፤ ሰሞ​ና​ቸ​ው​ንም ይጠ​ብቅ። ነገር ግን አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ይተው። እን​ዲሁ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”


跟着我们:

广告


广告