Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 44:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሳቱ ጊዜ ጣዖ​ታ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋ​ው​ያን ሳይ​ቀር ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ ‘እስራኤል እኔን ከመከተል በራቁ ጊዜ፣ ከእኔ የራቁትና ጣዖቶቻቸውን በመከተል የተቅበዘበዙት ሌዋውያን የኀጢአታቸውን ዕዳ ይሸከማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እስራኤል እኔን ከመከተል ርቀው በተቅበዘበዙ ጊዜ፥ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ የራቁት ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ከሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ ጋር እኔን ከድተው ለጣዖታት የሰገዱትን ሌዋውያንን እቀጣለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 44:10
20 交叉引用  

ቃየ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ኀጢ​አቴ ይቅር የማ​ት​ባል ታላቅ ናትን?


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም።


“አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?


እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ በጭንቅ የሚድን ከሆነ፥ ይልቁንስ ኃጥእና ዐመፀኛ በወዴት ይገለጣሉ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ው​ነቱ ሕማ​ምን ያርቅ ዘንድ ይወ​ዳል፤ ብር​ሃ​ን​ንም ያሳ​የ​ዋል፤ በጥ​በ​ቡም ይለ​የ​ዋል፤ ለጽ​ድ​ቅና ለበጎ ነገር የሚ​ገ​ዛ​ውን ጻድ​ቁን ያጸ​ድ​ቀ​ዋል። የብ​ዙ​ዎ​ች​ንም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን እርሱ ይደ​መ​ስ​ሳል።


“ነቢ​ዩና ካህ​ኑም ረክ​ሰ​ዋ​ልና፥ በቤ​ቴም ውስጥ ክፋ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይኸ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ደግሞ ከእኔ ርቀው እን​ዳ​ይ​ስቱ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ነው፤ እነ​ርሱ ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ካህ​ና​ቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም መካ​ከል ቅድ​ሳ​ቴን አረ​ከሱ፤ ከር​ኵ​ሰ​ትም አል​ራ​ቁም፤ በን​ጹ​ሕና በር​ኩስ መካ​ከል ያለ​ው​ንም ልዩ​ነት አላ​ወ​ቁም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከሰ​ን​በ​ታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ረከ​ስሁ።


በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ፊት አገ​ል​ግ​ለ​ዋ​ቸው ነበ​ሩና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት የኀ​ጢ​አት እን​ቅ​ፋት ሆነ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ እጄን በላ​ያ​ቸው አን​ሥ​ቻ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይሸ​ከ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የጠ​በቁ የሳ​ዶቅ ልጆች ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀ​ር​ባሉ፤ ስቡ​ንና ደሙ​ንም ወደ እኔ ያቀ​ርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋ​ው​ያን እንደ ሳቱ ላል​ሳ​ቱት፥ ሥር​ዐ​ቴን ለጠ​በ​ቁት፥ ከሳ​ዶቅ ልጆች ወገን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ካህ​ናት ይሆ​ናል።


እንደ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ካህኑ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የበ​ላ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አር​ክ​ሶ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፣ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል።


እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል፣ በሕግም ብዙ ሰዎችን አሰናክላችኋል፣ የሌዊንም ቃል ኪዳን አስነውራችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሌዋ​ው​ያን ግን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ይሥሩ፤ እነ​ር​ሱም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አይ​ወ​ር​ሱም።


ካህ​ኑም ይህን ሕግ ሁሉ ያደ​ር​ግ​ባ​ታል። ሰው​የ​ውም ከኀ​ጢ​አት ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ሴቲ​ቱም ኀጢ​አ​ቷን ትሸ​ከ​ማ​ለች።”


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


跟着我们:

广告


广告