ሕዝቅኤል 43:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ሰባት ቀንም በየዕለቱ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ከበጎችም አንድ ጠቦት በግ ያቀርባሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 “በየዕለቱ ለሰባት ቀን ተባዕት ፍየል ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለህ፤ ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፣ ከመንጋም የወጣውን አንድ አውራ በግ ይቅረብ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ሰባት ቀን በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ነውር የሌለባቸውን ከመንጋው አንድ ወይፈን ከመንጋው አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ሰባት ቀን ሙሉ በእያንዳንዱ ዕለት አንድ ፍየል፥ ከመንጋው አንድ ወይፈንና፥ አንድ የበግ አውራ፥ የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገህ ታቀርባለህ፤ እነዚህም ሁሉ ነውር የሌለባቸው መሆን አለባቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ሰባት ቀንም በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈን ከመንጋውም የወጣውን አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ። 参见章节 |