Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 43:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም እን​ዳ​ነ​ጹት እን​ዲሁ መሠ​ዊ​ያ​ውን ያነ​ጹ​በ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “በሁለተኛው ቀን እንከን የሌለበት ተባዕት ፍየል ወስደህ ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለህ፤ መሠዊያው በወይፈኑ እንደ ነጻ ሁሉ፣ በዚህም መንጻት አለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ በወይፈኑም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በማግስቱ ምንም ነውር የሌለበትን አንድ አውራ ፍየል ወስደህ የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገህ ታቀርበዋለህ፤ በኰርማውም ደም ባደረግኸው ዐይነት በፍየሉ ደም መሠዊያውን ታነጻለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፥ በወይፈኑም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 43:22
12 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


ከደ​ሙም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ በአ​ራቱ የመ​ሠ​ዊያ ቀን​ዶ​ቹም፥ በእ​ር​ከ​ኑም በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም በአ​ለው ክፈፍ ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እን​ዲሁ ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ታስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ት​ማ​ለህ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ውሰድ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም አንጻ።


“ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መባ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ቢሆን፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን፥ የፊት እግ​ሮ​ቹ​ንና ራሱን ጨምሮ ያቀ​ር​በ​ዋል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወዳ​ለው ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጥቶ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም፥ ከፍ​የ​ሉም ደም ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ያሉ​ትን ቀን​ዶች ያስ​ነ​ካል።


የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ከፍ​የ​ሎች ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያቀ​ር​ባል፤


ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


跟着我们:

广告


广告