ሕዝቅኤል 43:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እነርሱም ስለ ሠሩት ሥራ ሁሉ መቅሠፍታቸውን ያገኛሉ፤ አንተም የቤቱን መልክና ምሳሌውን፥ መውጫውንም፥ መግቢያውንም፥ ሥርዐቱንም፥ ሕጉንም ሁሉ አስታውቃቸው፤ ሥርዐቱንና ሕጉን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ፥ ያደርጉትም ዘንድ በፊታቸው ጻፈው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስላደረጉት ነገር ሁሉ ኀፍረት የሚሰማቸው ከሆነ፣ የቤተ መቅደሱን ንድፍ እንዲያውቁት አድርግ፤ ይኸውም አሠራሩን፣ መውጫና መግቢያውን፣ አጠቃላይ ንድፉን፣ ሥርዐቱንና ሕጉን ሁሉ ነው። ንድፉንና ሥርዐቱን እንዲጠብቁና እንዲከተሉ እነዚህን ሁሉ እነርሱ ባሉበት ጻፋቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በሠሩት ሥራ ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ፥ የቤቱን ንድፉንና አሠራሩን፥ መውጫውንና መግቢያውን፥ አጠቃላይ ንድፉን፥ ሥርዓቱን ሁሉ፥ ንድፉን ሁሉ፥ ሕጉን ሁሉ አሳውቃቸው፤ ንድፉን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ እንዲያዩትና እንዲያደርጉትም በፊታቸው ጻፈው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ባደረጉት ነገር ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ ስለ ቤተ መቅደሱ አሠራር ንድፍ፥ ስለ አደረጃጀቱ ስለ መውጫዎቹና ስለ መግቢያዎቹ፥ ስለ አጠቃላይ፥ አሠራሩ ሁኔታ፥ ስለ ሥነ ሥርዓቱ፥ ስለ ሕጎቹ ሁሉ አስረዳቸው፤ አጠቃላይ ንድፉን አጥንተው ሥርዓቱን ሁሉ ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ፊት ጻፈው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ከሠሩትም ሥራ ሁሉ የተነሣ ቢያፍሩ፥ የቤቱን መልክና ምሳሌውን መውጫውንም መግቢያውንም ሥርዓቱንም ሕጉንም ሁሉ አስታውቃቸው፥ ሥርዓቱንና ሕጉን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ ያደርጉትም ዘንድ በፊታቸው ጻፈው። 参见章节 |