Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 41:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በደጀ ሰላ​ሙም በሁ​ለቱ ወገን በዚ​ህና በዚያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶ​ችና የተ​ቀ​ረጹ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​በት፤ የመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎ​ችና የእ​ን​ጨቱ መድ​ረክ እን​ዲሁ ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በመተላለፊያ በረንዳውም ግራና ቀኝ ግንብ ላይ የዘንባባ ዛፍ ቅርጽ ያለባቸው ጠባብ መስኮቶች ነበሩ። ግራና ቀኝ ያሉት ክፍሎችም በደረጃው በኩል የሚሸፍን ጣራ ነበራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በመተላለፊያው በዚህና በዚያ ወገን ጠባብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት፤ የመቅደሱም ጓዳዎች ወፍራም ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በመግቢያው ክፍል ግድግዳዎች፥ በሁለቱም በኩል ወደ ውስጥ ገባ ያሉ መስኮቶች የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ የዓይነ ርግብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት፥ የመቅደሱም ጓዳዎችና የእንጨቱ መድረክ እንዲሁ ነበሩ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 41:26
7 交叉引用  

መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።


አዕ​ማ​ዱም ያሉ​በ​ትን ቤት ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ፊት ደግሞ ታላቅ አዕ​ማ​ድና መድ​ረክ ያሉ​በት ወለል ነበረ።


በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመ​ጣኝ፤ የደጀ ሰላ​ሙ​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፤ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም በዚህ ወገ​ንና በዚያ ወገን የነ​በ​ሩት ግን​ቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ።


የበ​ሩ​ንም ደጀ ሰላም ስም​ንት ክንድ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ደጀ ሰላም በስ​ተ​ው​ስጥ ነበረ።


መድ​ረ​ኮቹ፥ መስ​ኮ​ቶ​ቹና አዕ​ማዱ፥ በስ​ተ​ው​ስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላ​ሙም በእ​ን​ጨት ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በሦ​ስ​ቱም ዙሪያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ። መቅ​ደ​ሱም በመ​ድ​ረኩ አን​ጻር ከመ​ሬት ጀምሮ እስከ መስ​ኮ​ቶቹ ድረስ በእ​ን​ጨት ተለ​ብጦ ነበር፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም የዐ​ይነ ርግብ ነበሩ፤


የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ግንብ ስድ​ስት ክንድ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉ​ትን የጓ​ዳ​ዎ​ቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


跟着我们:

广告


广告