Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 በውስጠኛው አደባባይ፣ ከውስጠኛው በር ውጭ፣ ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ አንዱ በደቡብ ትይዩ በሰሜን በር በኩል ሲሆን፣ ሌላው በሰሜን ትይዩ በደቡብ በር በኩል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 በውስጠኛው መግቢያ በውጭው በኩል በውስጠኛው አደባባይ ለሚዘምሩ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ደቡብም ይመለከት ነበር፤ ሌላው ደግሞ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ከዚህም በኋላ ያ ሰው እኔን ወደ ውስጠኛው አደባባይ አስገባኝ፤ እዚያም ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ በሰሜን የቅጽር በር አጠገብ ወደ ደቡብ የሚያመለክት ሲሆን፥ ሁለተኛው በደቡብ የቅጽር በር አጠገብ ወደ ሰሜን የሚያመለክት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ፥ እነሆም፥ ሁለት ቤቶች ነበሩ፥ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ መግቢያውም ወደ ደቡብ ይመለከት ነበር፥ ሌላውም ወደ ደቡብ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ መግቢያውም ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:44
13 交叉引用  

የም​ሥ​ራ​ቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦ​ስ​ቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ በኩ​ልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።


ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜ​ኑና በም​ሥ​ራቁ በኩል በሌ​ላው በር አን​ጻር በር ነበረ፤ ከበ​ርም እስከ በር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በደ​ቡብ በኩል በር ነበረ፤ ከበር እስከ በር ድረስ በደ​ቡብ በኩል መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


በበ​ሮ​ቹም በግ​ንቡ አዕ​ማድ አጠ​ገብ ዕቃ ቤቱና መዝ​ጊ​ያው ነበሩ፤ በዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያጥቡ ነበር።


በዙ​ሪ​ያ​ውም በስ​ተ​ው​ስጥ የነ​በ​ረው የለ​ዘበ ከን​ፈ​ራ​ቸው አንድ ጋት ነበረ፤ በገ​በ​ታ​ውም ላይ መክ​ደኛ ነበረ፤ ከፀ​ሐ​ይና ከዝ​ና​ምም የተ​ሰ​ወረ ነበረ።


የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።


መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የተ​ቀ​ደሰ ማሕ​ሌ​ት​ንም አን​ብቡ፤ በል​ባ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀኙ፤ ዘም​ሩም።


በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ።


跟着我们:

广告


广告