Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እን​ደ​ዚ​ያም መጠን የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የዘብ ቤቶቹ፣ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው ከሌሎቹ ጋራ ተመሳሳይ ነበር፤ መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳዎቹ ዙሪያቸውን መስኮቶች ነበሯቸው፤ ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ጓዳዎቹ፥ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበራቸው፤ በእርሱና በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱ ደግሞ ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የዘብ ማረፊያ ክፍሎቹ፥ የግድግዳ ዐምዶቹና የመግቢያው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እንደዚያውም መጠን የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መዛነቢያዎቹንም ለካ፥ በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፥ ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:33
6 交叉引用  

መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።


በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


የዕቃ ቤቶ​ቹም በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግ​ንቡ አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ሳዩ ዘን​ባ​ባ​ዎ​ቹም አምሳ ክንድ ነበሩ፤ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ እንደ እነ​ዚያ መስ​ኮ​ቶች የሚ​መ​ስሉ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​በት፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告