Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወደ​ዚ​ያም አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም መልኩ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ናስ መልክ የመ​ሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእ​ጁም የተ​ልባ እግር ገመ​ድና የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ እር​ሱም በበሩ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወደዚያ ወሰደኝ፤ እነሆ መልኩ ናስ የሚመስል ሰው አየሁ፤ እርሱም የሐር ገመድና መለኪያ ዘንግ በእጁ ይዞ በመግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆ፥ መልኩ ናስ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወደዚያ ሲወስደኝም እንደ ነሐስ የሚያበራ መልክ ያለውን አንድ ሰው አየሁ፤ እርሱም ከበፍታ የተሠራ ገመድና መለኪያ ዘንግ ይዞ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆም፥ መልኩ እንደ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ፥ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:3
14 交叉引用  

ፍር​ዴን ለተ​ስፋ ይቅ​ር​ታ​ዬ​ንም ለት​ክ​ክ​ለኛ ሚዛን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በከ​ን​ቱና በሐ​ሰት የሚ​ታ​መኑ ከዐ​ውሎ ነፋስ አያ​መ​ል​ጡም።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


ከወ​ገ​ቡም አም​ሳያ ወደ ላይ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ የወ​ርቅ አም​ሳያ አየሁ፤ ከወ​ገ​ቡም አም​ሳያ ወደ ታች እንደ እሳት አም​ሳያ አየሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ።


እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእ​ግ​ራ​ቸው ሰኰና እንደ ላም እግር ሰኰና ነበረ፤ እንደ ተወ​ለ​ወለ ናስም ይብ​ለ​ጨ​ለጭ ነበር።


ወደ መቅ​ደ​ሱም አገ​ባኝ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድ​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ስድ​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከ​ተ​ውም በር ኋላ ቆመ፤ የም​ሥ​ራ​ቁን ወገን በመ​ለ​ኪያ ዘንግ አም​ስት መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


በመ​ቅ​ደ​ሱም ሆኖ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን ሰማሁ፤ በአ​ጠ​ገ​ቤም ሰው ቆሞ ነበር።


ሰው​ዮ​ውም የመ​ለ​ኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥ​ራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ቍር​ጭ​ም​ጭ​ሚት ደረሰ።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከወ​ገቡ በታች እንደ እሳት የሚ​መ​ስል የሰው አም​ሳያ ነበረ፤ ከወ​ገ​ቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ አይ​ነት ነበረ።


እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውሃዎች ድምፅ ነበረ።


በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።


የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።


跟着我们:

广告


广告