Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የዘብ ቤቶቹ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው ከሌሎቹ ጋራ ተመሳሳይ ነበር። መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳዎቹ ዙሪያቸውን መስኮቶች ነበሯቸው። ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጓዳዎቹ፥ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበራቸው፤ በእርሱና በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱ ደግሞ ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 የዘብ የማረፊያ ክፍሎቹ የግድግዳ ዐምዶቹና በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ስፋት እንደ ሌሎቹ ነበር፤ የበሩና የመተላለፊያው ርዝመት ኀምሳ ክንድ ወርዱም ኻያ አምስት ክንድ ነበር፤ በመተላለፊያውም ዙሪያ ሁሉ መስኮቶች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እንደዚያውም መጠን አድርጎ የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መዛነቢያዎቹንም ለካ፥ በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፥ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:29
15 交叉引用  

መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።


ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር።


ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።


ባሮ​ክም የኤ​ር​ም​ያ​ስን ቃል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በላ​ይ​ኛው አደ​ባ​ባይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በአ​ዲሱ በር መግ​ቢያ ባለው በጸ​ሓ​ፊው በሳ​ፋን ልጅ በገ​ማ​ርያ ክፍል በሕ​ዝቡ ሁሉ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ አን​በበ።


የም​ሥ​ራ​ቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦ​ስ​ቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ በኩ​ልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።


በዕቃ ቤቱም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ፥ በዚ​ያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ የዕቃ ቤቱም በዚህ በኩል ስድ​ስት ክንድ በዚ​ያም በኩል ስድ​ስት ክንድ ነበሩ።


በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ እንደ እነ​ዚያ መስ​ኮ​ቶች የሚ​መ​ስሉ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


እን​ደ​ዚ​ያም መጠን የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​በት፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告