Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የዕቃ ቤቶ​ቹም በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚ​ያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግ​ንቡ አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ሳዩ ዘን​ባ​ባ​ዎ​ቹም አምሳ ክንድ ነበሩ፤ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንደ መጀመሪያው በር ሁሉ ይኸኛውም በየጐኑ ያሉት ሦስት ሦስት የዘብ ቤቶች፣ በየመካከሉ ወጣ ወጣ ያሉ ግንቦችና መተላለፊያ በረንዳዎቹ መጠናቸው እኩል ነበር። ርዝመቱ ዐምሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ እንደ ፊተኛው በር መጠናቸው እኩል ነበር፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ግራና ቀኝ ያሉት ሦስቱ የዘብ ማረፊያ ክፍሎችና የግድግዳ ዐምዶች እንዲሁም በስተመጨረሻ ያለው ክፍል በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል ከታዩት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ልክ ነበራቸው፤ የቅጽር በሩ ጠቅላላ ርዝመት ኀምሳ ክንድ፥ ወርዱ ኻያ አምስት ክንድ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የዘበኛ ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ሦስት በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፥ የግንቡ አዕማድና መዛነቢያዎቹም እንደ ፊተኛው በር ልክ ነበሩ፥ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:21
8 交叉引用  

ወደ ደቡ​ብም መራኝ፤ እነ​ሆም ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት በር ነበረ፤ የግ​ን​ቡን አዕ​ማ​ድና መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም እን​ደ​ዚ​ያው መጠን አድ​ርጎ ለካ።


እን​ደ​ዚ​ያም መጠን የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በስተ ውጭ ወደ አለው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።


跟着我们:

广告


广告