Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ እዚያም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ክፍሎችና ድንጋይ የተነጠፈበት መመላለሻ አየሁ፤ በመመላለሻውም ዙሪያ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከዚያም ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፤ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚያ በኋላ ሰውዬው ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፤ በአደባባዩ ዙሪያ የድንጋይ ንጣፍና ክፍሎች ነበሩ ከንጣፉም ፊት ለፊት ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ወደ ውጭውም አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ዕቃ ቤቶችና ወለል ነበሩ፥ በወለሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:17
22 交叉引用  

በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።


የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ አጠ​ገብ በከ​ተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ በነ​በ​ረው በን​ጉሡ ጃን​ደ​ረባ በና​ታን መኖ​ሪያ አጠ​ገብ ለፀ​ሐይ የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ፈረ​ሶች አቃ​ጠለ፤ የፀ​ሐ​ይ​ንም ሰረ​ገ​ሎች በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


እነ​ዚህ አራቱ ኀያ​ላን ሰዎች ለአ​ራቱ በሮች ኀላ​ፊ​ዎች ነበሩ። ሌዋ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባሉ ጓዳ​ዎ​ችና ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የተ​ሾሙ ነበሩ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።


“ለድ​ን​ኳ​ኑም አደ​ባ​ባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተ​ሠሩ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም በደ​ቡብ በኩል ይሁኑ። የአ​ን​ዱም ወገን ርዝ​መት መቶ ክንድ ይሁን፤


የኪ​ሩ​ቤ​ልም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደ​ባ​ባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።


ወለ​ሉም በበ​ሮች አጠ​ገብ ነበረ፤ ይህም ታች​ኛው ወለል እንደ በሮቹ ርዝ​መት መጠን ነበረ።


በበ​ሮ​ቹም በግ​ንቡ አዕ​ማድ አጠ​ገብ ዕቃ ቤቱና መዝ​ጊ​ያው ነበሩ፤ በዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያጥቡ ነበር።


ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር።


ሰው​ዬ​ውም፥ “ይህ ወደ ደቡብ የሚ​መ​ለ​ከት ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው።


ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ።


በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል ወርዱ በቤቱ ዙሪያ ሁሉ ሃያ ክንድ ነበረ።


ጓዳ​ዎ​ቹም አንዱ ከአ​ንዱ በላይ በሦ​ስት ደርብ ነበሩ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳ​ዎች ነበሩ። በመ​ቅ​ደ​ሱም ግንብ ዙሪያ ደገ​ፋ​ዎች ይሆኑ ዘንድ አረ​ፍ​ቶች ነበሩ፤ ከመ​ቅ​ደሱ ግንብ ጋር ግን​አ​ል​ተ​ያ​ያ​ዙም ነበር።


በው​ጭም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜኑ መን​ገድ በም​ሥ​ራቅ በኩል አወ​ጣኝ፤ በል​ዩ​ውም ስፍራ አን​ጻ​ርና በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳ​ሉት አም​ስት ዕቃ ቤቶች አገ​ባኝ።


በደ​ቡ​ብም በኩል በል​ዩው ስፍ​ራና በግ​ቢው አን​ጻር ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሃ​ያው ክንድ አን​ጻር፥ በው​ጭ​ውም አደ​ባ​ባይ በወ​ለሉ አን​ጻር በሦ​ስት ደርብ በት​ይዩ የተ​ሠራ መተ​ላ​ለ​ፊያ ነበረ።


በዕቃ ቤቶ​ቹም ፊት በስ​ተ​ው​ስጥ ወርዱ ዐሥር ክንድ፥ ርዝ​መቱ መቶ ክንድ የሆነ መን​ገድ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከቱ ነበር።


ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በስተ ውጭ ወደ አለው ወደ መቅ​ደሱ በር መለ​ሰኝ፤ ተዘ​ግ​ቶም ነበር።


ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለሌ​ዋ​ው​ያን መኖ​ሪያ ርስት ከሃያ ዕቃ ቤቶች ጋር ይሆ​ናል።


በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አወ​ጣኝ፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ወዳ​ለው ወደ አራቱ ማዕ​ዘን አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ደ​ባ​ባዩ ማዕ​ዘን ሁሉ አደ​ባ​ባይ ነበረ።


በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው፤ አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።


跟着我们:

广告


广告