Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ደጀ ሰላ​ሙ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም ዙሪያ አደ​ባ​ባይ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በመግቢያው በር ዙሪያ ባሉት ወጣ ወጣ ባሉት ግንቦች ሁሉ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ ለካ፤ ስድሳ ክንድም ነበር። የተለካውም ከአደባባዩ ፊት ለፊት እስካለው መተላለፊያ በረንዳ ድረስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 መተላለፊያውን ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ፤ በበሩም መተላለፊያ ዙሪያ አደባባይ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በስተመጨረሻ ያለው ክፍል ወደ አደባባዩ ያመራ ነበር፤ እርሱም ሲለካ ኻያ ክንድ ሆኖ ተገኘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ደጀ ሰላሙንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ፥ በበሩም ደጀ ሰላም ዙሪያ አደባባይ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:14
11 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ልጅ ይሆ​ነኝ ዘንድ መር​ጬ​ዋ​ለ​ሁና፥ እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለ​ሁና ልጅህ ሰሎ​ሞን ቤቴ​ንና አደ​ባ​ባ​ዮ​ቼን ይሠ​ራል።


ጠማማ ልብም አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላ​ወ​ቅ​ሁም።


“ለድ​ን​ኳ​ኑም አደ​ባ​ባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተ​ሠሩ የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም በደ​ቡብ በኩል ይሁኑ። የአ​ን​ዱም ወገን ርዝ​መት መቶ ክንድ ይሁን፤


የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን መጋ​ረ​ጆች፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ንም፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ፤


ነገር ግን የሰ​በ​ሰ​ቡት ይበ​ሉ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፤ ያከ​ማ​ቹ​ት​ንም ወይን በመ​ቅ​ደሴ አደ​ባ​ባይ ላይ ይጠ​ጡ​ታል።


ከአ​ን​ዱም የዕቃ ቤት ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበ​ሩን ወርድ ሃያ አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በሩና በሩም ትይዩ ነበረ።


ከበ​ሩም መግ​ቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው የበሩ ደጀ ሰላም መጨ​ረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ።


የመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችም አራት ማዕ​ዘን ነበሩ፤ የመ​ቅ​ደሱ ፊትም መልኩ እን​ደ​ሌ​ላው መልክ ነበረ።


በው​ጭም አደ​ባ​ባይ በሰ​ሜኑ መን​ገድ በም​ሥ​ራቅ በኩል አወ​ጣኝ፤ በል​ዩ​ውም ስፍራ አን​ጻ​ርና በሰ​ሜን በኩል በአ​ለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳ​ሉት አም​ስት ዕቃ ቤቶች አገ​ባኝ።


ወደ አደ​ባ​ባ​ዩም መግ​ቢያ አስ​ገ​ባኝ፤ በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ በግ​ንቡ ውስጥ ፉካ ነበረ።


ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን አሮ​ንና ልጆቹ ይበ​ሉ​ታል፤ ቂጣ ሆኖ በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይበ​ላል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ባለው አደ​ባ​ባይ ይበ​ሉ​ታል።


跟着我们:

广告


广告