ሕዝቅኤል 40:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ከአንዱም የዕቃ ቤት ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሃያ አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፤ በሩና በሩም ትይዩ ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ከዚያም ከዘብ ቤቱ የኋላ ግድግዳ ጀምሮ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ያለውን የመግቢያ በር ለካ፤ ከአንዱ መከለያ ግድግዳ እስከ ሌላው መከለያ ግድግዳ ያለው ርቀት ሃያ ዐምስት ክንድ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ከአንዱ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩ ወርድ ሀያ አምስት ክንድ ሆነ፤ መዝጊያውና መዝጊያውም ትይዩ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ከዚያ በኋላ መግቢያውን ከአንዱ ማረፊያ ክፍል በስተጀርባ እስከ ሁለተኛው ማረፊያ ክፍል በስተጀርባ፥ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ ድረስ ለክቶ ኻያ አምስት ክንድ ሆኖ ተገኘ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ከአንዱም የዘበኛ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሀያ አምስት ክንድ አድርጎ ለካ፥ መዝጊያውና መዝጊያውም ትይዩ ነበረ። 参见章节 |