Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 40:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በተ​ማ​ረ​ክን በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ከወሩ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን፥ ከተ​ማ​ዪቱ ከተ​መ​ታች በኋላ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዚ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እር​ሱም ወደ​ዚያ ወሰ​ደኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በተሰደድን በሃያ ዐምስተኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በዐሥረኛው ቀን፣ ከተማዪቱ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበር፤ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በተሰደድን በሀያ አምስተኛው ዓመት፥ በዓመቱ መጀመሪያ፥ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ በተመታች በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፥ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በተሰደድን በሃያ አምስተኛው ዓመት፥ ኢየሩሳሌምም በጠላት እጅ በወደቀች በዐሥራ አራተኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፥ በዚያው ዕለት የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጥቶ ነበር፤ እርሱም ብድግ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደኝ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በተማረክን በሀያ አምስተኛው ዓመት በዓመቱ መጀመሪያ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ ከተመታች በኋላ በአሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 40:1
17 交叉引用  

ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ተና​ገሩ፤ በሉ​አ​ቸ​ውም፦ በዚህ ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአ​ባቱ ቤተ ሰቦች ቤቶች አንድ አንድ ጠቦት፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰውም ለራሱ ቤተ ሰብእ አንድ ጠቦት ይው​ሰድ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ሁሉ በሌ​ሊት ከግ​ብፅ ምድር ወጣ።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በፊ​ተ​ኛው ቀን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ትተ​ክ​ላ​ለህ።


መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በራ​እይ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎን ምድር ወደ ምር​ኮ​ኞቹ አመ​ጣኝ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


መን​ፈ​ስም አን​ሥቶ ወሰ​ደኝ፤ እኔም በም​ሬ​ትና በመ​ን​ፈሴ ሙቀት ሄድሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ በር​ትታ ነበር።


በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ እር​ሱም፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሜዳ ሂድ፤ በዚ​ያም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በተ​ማ​ረ​ክን በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተ​ማ​ዪቱ ተያ​ዘች አለኝ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈሱ አወ​ጣኝ፤ አጥ​ን​ቶ​ችም በሞ​ሉ​በት ሸለቆ መካ​ከል አኖ​ረኝ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤቴ ተቀ​ምጬ ሳለሁ፥ የይ​ሁ​ዳም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በፊቴ ተቀ​ም​ጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላዬ መጣ።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


跟着我们:

广告


广告