Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ደግ​ሞም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ጀራ በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በች​ግር እያሉ እን​ጀ​ራን በሚ​ዛን ይበ​ላሉ፥ እየ​ደ​ነ​ገ​ጡም ውኃን በልክ ይጠ​ጣሉ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ደግሞም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የኢየሩሳሌምን የምግብ ምንጭ አደርቃለሁ፤ ሕዝቡም የተወሰነ ምግብ በጭንቀት ይበላል፤ የተመጠነ ውሃም በሥጋት ይጠጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ እኔ በኢየሩሳሌም የምግብን በትር እሰብራለሁ፥ ምግብ እየፈሩ በሚዛን ይበላሉ፥ ውኃም እየደነገጡ በልክ ይጠጣሉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለኢየሩሳሌም የሚቀርበው ምግብ ሁሉ እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝብ በፍርሃትና በስጋት ተሞልተው የሚበሉትን እህልና የሚጠጡትን ውሃ እየመጠኑ እንዲመገቡና እንዲጠጡ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የኢየሩሳሌምን እንጀራ በትር እሰብራለሁ፥ እየፈሩም እንጀራን በሚዛን ይበላሉ፥ እየደነገጡም ውኃን በልክ ይጠጣሉ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 4:16
18 交叉引用  

በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ራብ ጸንቶ ነበ​ርና ለሀ​ገሩ ሰዎች እህል ታጣ።


በሰ​ማ​ር​ያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነ​ሆም፥ የአ​ህያ ራስ በኀ​ምሳ ብር፥ የድ​ርጎ አንድ አራ​ተኛ የሚ​ሆን ኵስሐ ርግ​ብም በአ​ም​ስት ብር እስ​ኪ​ሽጥ ድረስ ከበ​ቡ​አት።


ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።


በጠ​ላት ፊት ጽኑ ግንብ ነህ፤ ተስ​ፋ​ዬም ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና መራ​ኸኝ።


እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ከይ​ሁዳ ኀይ​ለ​ኛ​ውን ወን​ድና ኀይ​ለ​ኛ​ዋን ሴት፥ የእ​ን​ጃ​ራን ኀይል ሁሉ፥ የው​ኃ​ው​ንም ኀይል ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ወር በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀ​ገ​ሩም ሰዎች እን​ጀራ ታጣ።


ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።


ውኃ​ች​ንን በገ​ን​ዘብ ጠጣን፤ እን​ጨ​ታ​ችን በዋጋ በት​ከ​ሻ​ችን ይመ​ጣል።


ከም​ድረ በዳ ሰይፍ የተ​ነሣ፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እን​ጀ​ራ​ች​ንን እና​መ​ጣ​ለን።


“የሰው ልጅ ሆይ! ምድር ብት​በ​ድ​ለኝ፥ ብት​ስት፥ ኀጢ​አ​ትም ብት​ሠራ እጄን በእ​ር​ስዋ አነ​ሣ​ለሁ፤ የእ​ህ​ሉ​ንም ኀይል አጠ​ፋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ረሀ​ብን እል​ካ​ለሁ፤ ከብ​ቱ​ንና ሰዉ​ንም ከእ​ር​ስዋ አጠ​ፋ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “እነሆ በሰው ኵስ ፋንታ የከ​ብት ኩበት ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ጀ​ራ​ህን ትጋ​ግ​ራ​ለህ” አለኝ።


ለማ​ጥ​ፋ​ትም የሆ​ነ​ውን፥ አጠ​ፋ​ች​ሁም ዘንድ የም​ሰ​ድ​ደ​ውን የራብ ፍላጻ በላ​ያ​ችሁ በሰ​ደ​ድሁ ጊዜ፥ ራብን እጨ​ም​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ የእ​ን​ጀ​ራ​ች​ሁ​ንም በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ።


በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።


የሁ​ለት ወይም የሦ​ስት ከተ​ሞች ሰዎች ወደ አን​ዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አል​ረ​ኩም፤ እና​ንተ ግን ወደ እኔ አል​ተ​መ​ለ​ሳ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።


跟着我们:

广告


广告