Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 39:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የኀ​ያ​ላ​ኑን ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አለ​ቆች፥ የአ​ውራ ፍየ​ሎ​ች​ንና የአ​ውራ በጎ​ችን፥ የወ​ይ​ፈ​ኖ​ች​ንና፥ የባ​ሳ​ንን ፍሪ​ዳ​ዎች ሁሉ፥ ደም ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንደ አውራ በግና እንደ ጠቦት፤ እንደ ፍየልና እንደ ወይፈን፣ የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም መሳፍንት ደም ትጠጣላችሁ፤ እነዚህ ሁሉ የሠቡ የባሳን ከብቶች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የኃያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ፥ የምድር አለቆችን፥ የአውራ በጎችንና የጠቦቶችን፥ የፍየሎችንና የወይፈኖችን፥ የባሻንን ፍሪዳዎች ሁሉ ደም ትጠጣላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንደ ቅልብ የባሳን ጠቦትና ሙክት ፍየልና ኰርማ የሆኑትን የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድር ልዑላንንም ደም ትጠጣላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የኃያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ የምድርንም አለቆች፥ የአውራ በጎችንና የጠቦቶችን፥ የፍየሎችንና የወይፈኖችን፥ የባሳንን ፍሪዳዎች ሁሉ፥ ደም ትጠጣላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 39:18
16 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በዝ​ማሬ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በም​ስ​ጋ​ናም ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በባ​ሶራ፥ ታላ​ቅም እርድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በበግ ስብ፥ በፍ​የል ደምም፥ በአ​ው​ራም በግ ስብ ወፍ​ራ​ለች።


ኀያ​ላን ከእ​ነ​ርሱ ጋር፥ ወይ​ፈ​ኖ​ችም ከኮ​ር​ማ​ዎች ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም በደም ትሰ​ክ​ራ​ለች፤ በስ​ባ​ቸ​ውም ትወ​ፍ​ራ​ለች።


ፈር​ተው ወደ ኋላ ሲመ​ለሱ፥ ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሲደ​ክሙ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ሳይ​መ​ለ​ከቱ ፈጥ​ነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ይከ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤


ፍሬ​ዋን ሁሉ አድ​ር​ቁ​ባት፤ ወደ መታ​ረ​ድም ይው​ረዱ፤ ቀና​ቸው ደር​ሳ​ለ​ችና፥ እነ​ሱን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ወዮ​ላ​ቸው!


እንደ ጠቦ​ቶ​ችና እንደ አውራ በጎች፥ እንደ አውራ ፍየ​ሎ​ችም ወደ መታ​ረድ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አን​ተ​ንና የወ​ን​ዞ​ች​ህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥ​ላ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ እንጂ አት​ከ​ማ​ችም፤ አት​ሰ​በ​ሰ​ብ​ምም፤ መብ​ልም አድ​ርጌ ለም​ድር አራ​ዊ​ትና ለሰ​ማይ ወፎች ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ን​ተም መን​ጋዬ ሆይ! እነሆ በበ​ግና በበግ መካ​ከል፥ በአ​ውራ በግና በአ​ውራ ፍየ​ልም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረ​ኞች ስለ​ሌሉ፥ እረ​ኞ​ችም በጎ​ችን ስላ​ል​ፈ​ለጉ፥ እረ​ኞ​ችም ራሳ​ቸ​ውን እንጂ በጎ​ችን ስላ​ላ​ሰ​ማሩ፥ በጎች ንጥ​ቂያ ሆነ​ዋ​ልና፥ በጎ​ችም ለዱር አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆነ​ዋ​ልና፤


እኔም ከማ​ር​ድ​ላ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕት እስ​ክ​ት​ጠ​ግቡ ድረስ ጮማን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እስ​ክ​ት​ሰ​ክ​ሩም ድረስ ደምን ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።


በሰ​ማ​ርያ ተራራ የም​ት​ኖሩ፥ ድሆ​ች​ንም የም​ት​በ​ድሉ፥ ችግ​ረ​ኞ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጌቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም፦ አምጡ እን​ጠጣ የም​ትሉ እና​ንተ የባ​ሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።


በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።


የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።


跟着我们:

广告


广告