Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 39:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “በዚ​ያም ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በባ​ሕር ምሥ​ራቅ የሚ​ያ​ል​ፉ​በ​ትን ሸለቆ፥ የመ​ቃ​ብ​ርን ስፍራ ለጎግ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ል​ፉ​ት​ንም ይከ​ለ​ክ​ላል፤ በዚ​ያም ጎግ​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ይቀ​ብ​ራሉ፤ የሸ​ለ​ቆ​ው​ንም ስም የጎግ መቃ​ብር ብለው ይጠ​ሩ​ታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ ‘በዚያ ቀን ሰዎች በምሥራቅ በኩል ወደ ባሕሩ በሚጓዙበት ሸለቆ፣ ለጎግ የመቃብር ስፍራ በእስራኤል እሰጠዋለሁ። ጎግና ሰራዊቱ ሁሉ በዚያ ስለሚቀበሩ፣ የተጓዦችን መንገድ ይዘጋሉ፤ ስለዚህም የሐሞን ጎግ ሸለቆ ይባላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ በእስራኤል ምድር በሚገኘው፥ ከሙት ባሕር በስተ ምሥራቅ ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ውስጥ፥ ለጎግ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ከብዛቱ የተነሣ መተላለፊያ መንገዱን ይዘጋል፤ ጎግና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ይቀበራሉ፤ ስለዚህም ያ ሸለቆ ‘የጎግ ሠራዊት ሸለቆ’ ተብሎ ይጠራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል፥ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ፥ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 39:11
10 交叉引用  

እንደ ክም​ርም አድ​ር​ገው ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ምድ​ርም ገማች።


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊት​ህን በጎግ ላይና በማ​ጎግ ምድር ላይ፥ በሮስ በሞ​ሳ​ሕና በቶ​ቤል አለቃ ላይ አቅ​ና​በት፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገ​ር​በት፤


እን​ጨ​ትን ከሜዳ አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ከዱ​ርም አይ​ቈ​ር​ጡም፤ ነገር ግን የጦር መሣ​ሪ​ያን በእ​ሳት ያነ​ድ​ዳሉ፤ የገ​ፈ​ፉ​አ​ቸ​ው​ንም ይገ​ፍ​ፋሉ፤ የበ​ዘ​በ​ዙ​አ​ቸ​ው​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛሉ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ምድ​ር​ንም ያነ​ደዱ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰባት ወር መቃ​ብር እየ​ቈ​ፈሩ ይቀ​ብ​ሯ​ቸ​ዋል፤


በም​ድ​ርም የሚ​ዞ​ሩት ያል​ፋሉ፤ የሰ​ው​ንም አጥ​ንት ቢያዩ፥ ቀባ​ሪ​ዎች በጎግ መቃ​ብር ሸለቆ እስ​ኪ​ቀ​ብ​ሩት ድረስ ምል​ክት ያኖ​ሩ​በ​ታል።


የም​ሥ​ራ​ቁም ድን​በር በሐ​ው​ራን በደ​ማ​ስ​ቆና በገ​ለ​ዓድ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምድር መካ​ከል ዮር​ዳ​ኖስ ይሆ​ናል። ከሰ​ሜኑ ድን​በር ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የም​ሥ​ራቁ ድን​በር ይህ ነው።


የጐ​መጁ ሕዝብ በዚያ ተቀ​ብ​ረ​ዋ​ልና የዚያ ስፍራ ስም “መቃ​ብረ ፍት​ወት” ተብሎ ተጠራ።


ዳር​ቻ​ውም ከሴ​ፋማ በዐ​ይን ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ወደ አር​ቤላ ይወ​ር​ዳል፤ እስከ ኬኔ​ሬት የባ​ሕር ወሽ​መጥ በም​ሥ​ራቅ በኩል ይደ​ር​ሳል፤


ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር።


ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告