Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እመ​ል​ስ​ህ​ማ​ለሁ፤ በመ​ን​ጋ​ጋ​ህም ልጓም አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ሠራ​ዊ​ት​ህን ሁሉ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ የጦር ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን፥ ሰይ​ፍ​ንም የያ​ዙ​ትን ሁሉ አወ​ጣ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ መንጋጋህ ውስጥ መንጠቆ አስገብቼ ከመላው ሰራዊትህ ጋራ፣ ፈረሶችህን፣ ፈረሰኞችህን ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ትልቅና ትንሽ ሰይፍ የያዙትን ሁሉ፣ ሰይፋቸውንም የወለወሉትን ሁሉ አስወጣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፥ መንጠቆ በመንጋጋህ አስገባሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህን ሁሉ፥ ፈረሶችን፥ ፈረሰኞችን፥ የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ሁሉም ሰይፍ የያዙ ጋሻና ራስ ቁርን ካደረጉ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በመንጋጋው መንጠቆ አስገብቼ በመጐተት እርሱንና ሠራዊቱን ወደ መጡበት ወደ ኋላቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ሠራዊቱ ከፈረሶችና የጦር ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞቹ ጋር እጅግ የበዛ ነው፤ እያንዳንዱ ወታደር ትልቅና ትንሽ ጋሻ አንግቦ ሰይፍ ታጥቆአል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:4
14 交叉引用  

ቍጣ​ህና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ስለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።


ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ውስጥ ባለ​ችው በአ​ን​ባ​ዪቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነ​ዚህ ጋሻና ጦር የሚ​ይዙ፥ ጽኑ​ዓን፥ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ አን​በሳ ፊት ነበረ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ደ​ሚ​ዘ​ልል ሚዳቋ ፈጣ​ኖች ነበሩ።


ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ ሰበ​ሰበ፤ እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አቆ​ማ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁሉ የሽህ አለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ችን አደ​ረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰ​ል​ፍም የሚ​ወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚ​ይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎ​ችን አገኘ።


የተ​ቈ​ጣ​ኸው ቍጣና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ሰለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በ​ትም መን​ገድ እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና ፈረ​ሱን ሠራ​ዊ​ቱ​ንና አር​በ​ኛ​ውን ያወ​ጣል፤ እነ​ርሱ ግን በአ​ን​ድ​ነት ተኝ​ተ​ዋል፤ አይ​ነ​ሡም፤ ቀር​ተ​ዋል፤ እንደ ጥዋፍ ኩስ​ታ​ሪም ጠፍ​ተ​ዋል፤


በፈ​ረ​ሶች ተቀ​መጡ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንም አዘ​ጋ​ጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚ​ያ​ነ​ግቡ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያና የሊ​ብያ ኀያ​ላን፥ ቀስ​ት​ንም ይዘው የሚ​ስቡ የሉድ ኀያ​ላን ይውጡ።


የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ጌጠኛ ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን፥ በፈ​ረ​ሶች ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁሉ​ንም መልከ መል​ካ​ሞ​ችን ጐበ​ዛ​ዝት አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


በመ​ን​ጋ​ጋ​ዎ​ችህ መቃ​ጥን አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህ​ንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ አጣ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ከወ​ን​ዞ​ች​ህም መካ​ከል አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ ይጣ​በ​ቃሉ።


አን​ተም፥ ከአ​ን​ተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላ​ቸው በፈ​ረ​ሶች ላይ የተ​ቀ​መጡ፥ ታላቅ ወገ​ንና ብርቱ ሠራ​ዊት፥ ከሰ​ሜን ዳርቻ ከስ​ፍ​ራ​ችሁ ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሮስ፥ የሞ​ሣ​ሕና የቶ​ቤል አለቃ ጎግ ሆይ! እነሆ! እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ።


እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እመ​ራ​ሃ​ለሁ፤ ከሰ​ሜ​ንም ዳርቻ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እወ​ስ​ድ​ሃ​ለሁ።


ከማ​ዕ​ዴም ከፈ​ረ​ሶ​ችና ከፈ​ረ​ሰ​ኞች፥ ከኀ​ያ​ላ​ንና ከሰ​ል​ፈ​ኞች ሁሉ ሥጋን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ አግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እና​ን​ተን በሰ​ልፍ ዕቃ፥ ቅሬ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ቃ​ጥን የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን እነሆ በላ​ያ​ችሁ ይመ​ጣል” ብሎ በቅ​ዱ​ስ​ነቱ ምሎ​አል።


跟着我们:

广告


广告