ሕዝቅኤል 38:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ምርኮን ትማርክ ዘንድ፥ ብዝበዛንም ትበዘብዝ ዘንድ፥ ባድማም በነበሩ፥ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም በአገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትመልሳለህ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 እዘርፋለሁ፤ እነጥቃለሁ፤ እንዲሁም ከአሕዛብ ተሰባስቦ እንደ ገና በሰፈረው፣ በከብትና በሸቀጥ በከበረው፣ በምድሪቱም መካከል በሚኖረው ሕዝብ ላይ እጄን አነሣለሁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ምርኮን ልትማርክ፥ ብዝበዛን ልትበዘብዝ፤ ባድማም በነበሩ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም ባገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ከሕዝቦች መካከል የተመለሱትም ሰዎች በምድር እምብርት ላይ ይኖራሉ፤ እነርሱም እንስሶችና ቈሳቊስ አሉአቸው። ባድማ የነበረችውም ምድር አሁን የሰው መኖሪያ ሆናለች፤ ሐሳቤ ምርኮን ለመማረክና ለመውሰድ፥ እንዲሁም በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ምርኮን ትማርክ ዘንድ ብዝበዛንም ትበዘብዝ ዘንድ፥ ባድማም በነበሩ አሁንም ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከአሕዛብም በተሰበሰበ፥ ከብትና ዕቃንም ባገኘ፥ በምድርም መካከል በተቀመጠ ሕዝብ ላይ እጅህን ትዘረጋ ዘንድ። 参见章节 |