Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 37:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “በእ​ነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ እና​ንተ የደ​ረ​ቃ​ችሁ አጥ​ን​ቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለእነዚህ ዐጥንቶች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘እናንተ ደረቅ ዐጥንቶች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የጌታን ቃል ሰሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እርሱም እንዲህ አለ፦ “ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ብለህ ትንቢት ተናገር፦ እናንተ ደረቅ አጥንቶች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 37:4
17 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ፥ “መሠ​ዊያ ሆይ፥ መሠ​ዊያ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮ​ስ​ያስ የሚ​ባል ልጅ ለዳ​ዊት ቤት ይወ​ለ​ዳል፤ ዕጣ​ንም የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ብ​ህን የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹን ካህ​ናት ይሠ​ዋ​ብ​ሃል፤ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት ያቃ​ጥ​ል​ብ​ሃል” ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጠራ።


ቍር​በ​ትና ሥጋን አለ​በ​ስ​ኸኝ፤ በአ​ጥ​ን​ትና በዥ​ማ​ትም አጠ​ነ​ከ​ር​ኸኝ።


ሙታን ይነ​ሣሉ፤ በመ​ቃ​ብር ያሉም ይድ​ናሉ። በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ከአ​ንተ የሚ​ገኝ ጠል መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ነውና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምድር ታጠ​ፋ​ለህ።


እና​ንተ ደን​ቆ​ሮች፥ ስሙ፤ እና​ን​ተም ዕው​ሮች እዩ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም።


ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ትን​ቢት ተና​ገር፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ በላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል።


ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ! እነሆ መቃ​ብ​ራ​ች​ሁን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከመ​ቃ​ብ​ራ​ች​ሁም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋስ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋ​ስም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአ​ራቱ ነፋ​ሳት ዘንድ ና፤ እነ​ዚህ ሙታን በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በል​ባ​ቸው በል” አለኝ።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።


“ይህ​ችን በት​ር​ህን ውሰድ፤ አን​ተና ወን​ድ​ምህ አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን ሰብ​ስቡ፤ ዐለ​ቷ​ንም በፊ​ታ​ቸው እዘ​ዟት፤ ውኃ ትሰ​ጣ​ለች፤ ከድ​ን​ጋ​ይ​ዋም ውኃ ታወ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ማኅ​በ​ሩን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታጠ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”


ኢየሱስም መልሶ “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ብትሉት ይሆናል፤


እና​ቱም ለአ​ሳ​ላ​ፊ​ዎቹ፥ “የሚ​ላ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ርጉ” አለ​ቻ​ቸው።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል፤” ተባልሁ።


跟着我们:

广告


广告