ሕዝቅኤል 37:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አባቶቻችሁም በኖሩባት፤ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው፥ የልጅ ልጆቻቸውም ለዘለዓለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘለዓለም አለቃ ይሆናቸዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 አባቶቻችሁ በኖሩበት፣ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት ምድር ይኖራሉ። በዚያም እነርሱ፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘላለም ይኖራሉ፤ ባሪያዬ ዳዊትም ለዘላለም ንጉሣቸው ይሆናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 አባቶቻችሁም በኖሩባት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፥ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፥ ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል። 参见章节 |