Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! ሕዝቤ ይመጡ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ሉና ወይ​ና​ች​ሁ​ንና ፍሬ​ያ​ች​ሁን ይበ​ላሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ግን፤ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቅርንጫፍ ታወጣላችሁ፤ ፍሬም ታፈራላችሁ፤ በቅርቡ ወደ አገራቸው ይመለሳሉና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እናንተም የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ ቅርንጫፎችን ታቆጠቁጣላችሁ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ ለመምጣት ቀርበዋልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለ እናንተ ስለ ሕዝቤ እስራኤል ግን የምለው ይህ ነው፤ በእስራኤል ተራራዎች ላይ የሚገኙ ዛፎች ሁሉ እንደገና ይለመልማሉ፤ ፍሬም ይሰጡአችኋል፤ እናንተም በፍጥነት ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ እናንተ ግን ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ይመጡም ዘንድ ቀርበዋልና ለሕዝቤ ለእስራኤል ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:8
17 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቸ​ኞ​ችን በቤቱ ያሳ​ድ​ራ​ቸ​ዋል፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም በኀ​ይሉ ያወ​ጣ​ቸ​ዋል፤ በመ​ቃ​ብር የሚ​ኖሩ ኀዘ​ን​ተ​ኞ​ች​ንም እን​ዲሁ።


አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ በልቤ ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ። ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስም​ህን አከ​ብ​ራ​ለሁ፤


በሚ​መ​ጣው ዘመን የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሥር ይሰ​ድ​ዳሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ያብ​ባል፤ በፍ​ሬ​ያ​ቸ​ውም የዓ​ለ​ሙን ፊት ይሞ​ላሉ።


በም​ድ​ርም ለተ​ዘ​ራው ዘርህ ዝናም ይዘ​ን​ማል፤ ከም​ድ​ርም ፍሬ የሚ​ወጣ እን​ጀራ ወፍ​ራ​ምና ብዙ ይሆ​ናል። በዚ​ያም ቀን ከብ​ቶ​ችህ በሰ​ፊና በለ​መ​ለመ መስክ ይሰ​ማ​ራሉ፤


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ረ​ፉ​ትን ያከ​ብ​ርና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ በጌ​ት​ነቱ ምክር በም​ድር ላይ ያበ​ራል።


የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘርና የይ​ሁ​ዳን ዘር አመ​ጣ​ለሁ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ፤ እኔ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸ​ውና ባሪ​ያ​ዎ​ችም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በዚ​ያም ይኖ​ራሉ።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የም​ና​ገ​ረ​ውም ቃል ይፈ​ጸ​ማል፤ ደግ​ሞም አይ​ዘ​ገ​ይም፤ እና​ንተ ዐመ​ፀኛ ቤት ሆይ! በዘ​መ​ና​ችሁ ቃሌን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ጽ​መ​ው​ማ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ንም ያወ​ጣል፤ ፍሬም ያፈ​ራል፤ ታላ​ቅም ዝግባ ይሆ​ናል፤ በበ​ታ​ቹም ወፎች ሁሉ ያር​ፋሉ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ቹም ጥላ በክ​ንፍ የሚ​በ​ርር ሁሉ ይጠ​ጋል፤ ቅር​ን​ጫ​ፉም ይሰ​ፋል።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ በአሉ አሕ​ዛብ ላይ እኔ እጄን አነ​ሣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።


እና​ንተ የም​ድር እን​ስ​ሶች ሆይ! የም​ድረ በዳው ማሰ​ማ​ርያ ለም​ል​ሞ​አ​ልና፥ ዛፉም ፍሬ​ውን አፍ​ር​ቶ​አ​ልና፥ በለ​ሱና ወይ​ኑም ኀይ​ላ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋ​ልና አት​ፍሩ።


ዐው​ድ​ማ​ዎ​ችም እህ​ልን ይሞ​ላሉ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ዎ​ችም የወ​ይን ጠጅ​ንና ዘይ​ትን አት​ረ​ፍ​ር​ፈው ያፈ​ስ​ሳሉ።


ፍጹ​ም​ነ​ታ​ች​ሁም በሰው ሁሉ ዘንድ ይታ​ወቅ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅርብ ነው፤


“ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ፈጥኖ ይደ​ር​ሳል፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም።


跟着我们:

广告


广告