Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ደግሞ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይሹ​ኛል፤ ሰው​ንም እንደ መንጋ አበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እንደ ገና ለእስራኤል ቤት ልመና ዕሺ እላለሁ፤ ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ ሕዝባቸውን እንደ በግ መንጋ አበዛዋለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁንም የእስራኤል ቤት እንድሠራላቸው እንዲፈልጉኝ እፈቅድላቸዋለሁ፥ ሰዎችንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስራኤላውያን ደግመው አንድ ጊዜ ይህን እንዲለምኑኝ አደርጋለሁ፤ ቊጥራቸውንም እንደ በጎች መንጋ አበዛዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:37
23 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ግን ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም በሚ​ፈ​ሩት ላይ፥ ጽድ​ቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤


ከእ​ር​ሱም ዘንድ የም​ስ​ጋ​ናና የዘ​ፈን ድምፅ ይወ​ጣል፤ እኔም አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አያ​ን​ሱ​ምም።


“የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ ሰዎች በል​ባ​ቸው ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አኑ​ረ​ዋል፤ የበ​ደ​ላ​ቸ​ው​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊ​ታ​ቸው አቁ​መ​ዋል፤ እኔስ ለእ​ነ​ርሱ መልስ ልመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ውን?


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ትጠ​ይቁ ዘንድ መጥ​ታ​ች​ኋ​ልን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ቍር​ባ​ና​ች​ሁን በአ​ቀ​ረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም በእ​ሳት ባሳ​ለ​ፋ​ችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐ​ሳ​ባ​ችሁ ሁሉ ረከ​ሳ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አል​መ​ል​ስ​ላ​ች​ሁም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም የቀ​ሩት አሕ​ዛብ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ረ​ሱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆ​ነ​ው​ንም እንደ ተከ​ልሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፥ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እንደ ተቀ​ደሱ በጎች፥ በበ​ዓ​ላ​ቶ​ችዋ ቀን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በጎች እን​ዲሁ የፈ​ረ​ሱት ከተ​ሞች በሰ​ዎች መንጋ ይሞ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ያዕቆብ ሆይ፥ ሁልንተናህን ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልንም ቅሬታ ፈጽሞ አከማቻለሁ፥ እንደ ባሶራ በጎችና እንደ መንጋ በማሰማርያቸው ውስጥ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፥ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።


ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፣ አደላድላቸዋለሁም፣ እመልሳቸዋለሁ፣ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።


በአሕዛብም መካከል ብዘራቸው እንኳ በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል፥ ከልጆቻቸውም ጋር በሕይወት ይኖራሉ፥ ይመለሱማል።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


አባ​ቶ​ች​ህም ወደ ወረ​ሱ​አት ምድር አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ ትወ​ር​ሳ​ት​ማ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ነገር ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ይልቅ ያበ​ዛ​ሃል።


በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ።


እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።


跟着我们:

广告


广告