ሕዝቅኤል 36:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 በዙሪያችሁም የቀሩት አሕዛብ፥ እኔ እግዚአብሔር የፈረሱትን ስፍራዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆነውንም እንደ ተከልሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ከዚያም በዙሪያችሁ የነበሩ የቀሩት አሕዛብ ፈርሶ የነበረውን መልሼ የሠራሁ፣ ጠፍ የነበረውን ያለመለምሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እኔም አደርገዋለሁ።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 በዙሪያችሁም የቀሩት መንግሥታት፥ የፈረሱትን ስፍራዎች የሠራሁ፥ ባድማ የሆነውንም የተከልሁ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 በዚያን ጊዜ ከጥፋት የተረፉት የጐረቤት አገሮች ሕዝብ ሁሉ የፈረሱ ከተሞችን መልሼ የሠራሁና ባድማ የሆነውን ቦታ ያለመለምኩ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ እንደምፈጽም ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም እፈጽመዋለሁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 በዙሪያችሁም የቀሩት አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር የፈረሱትን ስፍራዎች እንደ ሠራሁ ውድማ የሆነውንም እንደ ተከልሁ ያውቃሉ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ። 参见章节 |