Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም ክፉ መንገዳችሁንና የረከሰ ሥራችሁን ታስታውሳላችሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁና ስለ አስጸያፊ ድርጊታችሁ ራሳችሁን ትጠላላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ክፉዎች መንገዶቻችሁንና መልካም ያልሆኑ ሥራዎቻችሁን ታስባላችሁ፥ ስለ በደሎቻችሁና ስለ ርኩሰቶቻችሁም ራሳችሁን ትጠላላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 መጥፎ ጠባያችሁንና ትፈጽሙት የነበረውንም ክፉ ሥራ ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በኃጢአታችሁና ትፈጽሙት በነበረው የረከሰ ሥራ ምክንያት ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፥ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:31
17 交叉引用  

ስለ​ዚህ ራሴን እን​ቃ​ለሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ቀለጠ። እኔ አፈ​ርና አመድ እንደ ሆንሁ አው​ቃ​ለሁ።”


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል።


በዚ​ያም የረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ባ​ትን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁን ሁሉ ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ በፊ​ታ​ች​ሁም አይ​ታ​ችሁ ስለ ሠራ​ች​ሁት ክፋ​ታ​ችሁ ሁሉ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ።


እኔ ደግሞ እጄን በእጄ ላይ አጨ​በ​ጭ​ባ​ለሁ፤ መዓ​ቴ​ንም እል​ካ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”


በም​ድ​ራ​ቸው ተዘ​ል​ለው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና የበ​ደ​ሉ​ኝን በደ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ ይሸ​ከ​ማሉ፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ቸ​ውም የለም።


በዚያ በተ​ማ​ረ​ኩ​በት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከእ​ና​ንተ የዳ​ኑት ያስ​ቡ​ኛል፤ ለሰ​ሰ​ኑ​በት፥ ከእ​ኔም ለራ​ቁ​በት ለል​ቡ​ና​ቸው፥ ለሰ​ሰኑ፥ ጣዖ​ት​ንም ለተ​ከ​ተሉ ለዓ​ይ​ኖ​ቻ​ቸው ማልሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ እን​ዳ​መ​ለኩ መጠን ስለ ሥራ​ቸው ክፋት ፊታ​ቸ​ውን ይነ​ጫሉ።


ከእ​ና​ን​ተም ተለ​ይ​ተው የቀ​ሩት ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይጠ​ፋሉ፤ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ደግሞ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ይቀ​ል​ጣሉ።


ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያ​ነሣ አል​ወ​ደ​ደም፤ ደረ​ቱ​ንም እየ​መታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢ​ኣ​ተ​ኛ​ውን ይቅር በለኝ’ አለ።


በዚ​ያን ጊዜ ሥራ​ች​ሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍ​ሩ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ መጨ​ረ​ሻው ሞት ነውና።


跟着我们:

广告


广告