Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉ አሕ​ዛብ አዋ​ር​ደ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ውጠ​ዋ​ች​ሁ​ማ​ልና፥ እና​ን​ተም የተ​ና​ጋ​ሪ​ዎች ከን​ፈር መተ​ረ​ቻና የአ​ሕ​ዛብ ማላ​ገጫ ሆና​ች​ኋ​ልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከየአቅጣጫው ከብበው በመውጋት ስላጠቋችሁ፣ ለቀሩት ሕዝቦች ሁሉ ርስት ሆናችሁ፤ ለሕዝብም መሣቂያና መሣለቂያ ሆናችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላጠፉአችሁ፥ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችኋልምና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብለህ ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር አለኝ፦ የባዕድ አገር ሕዝቦች በሁሉም አቅጣጫ ምድራችሁን ስላፈራረሱትና በእርግጥም ባድማ ስላደረጉት አገራችሁ ለሌሎች ሕዝቦች ንብረት ሆነ። እናንተም የሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆናችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:3
33 交叉引用  

ነፍሴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ገዛ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? መድ​ኀ​ኒቴ ከእ​ርሱ ዘንድ ናትና።


ጥላዋ ተራ​ሮ​ችን ከደነ፥ ጫፎ​ች​ዋም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝግባ ሆኑ።


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ በባ​ሪ​ያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈ​ጣ​ለህ?


በሕይወት ሳለ እንደ ሲኦል እንዋጠው፥ መታሰቢያውንም ከምድር እናጥፋ፤


ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።


የአ​ን​በሳ ደቦ​ሎች በእ​ርሱ ላይ አገሡ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ደነፉ፤ ምድ​ሩ​ንም ባድማ አደ​ረጉ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸ​ውም የለም።


በማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም ስፍራ ሁሉ ለስ​ድ​ብና ለም​ሳሌ፥ ለጥ​ላ​ቻና ለር​ግ​ማን ይሆኑ ዘንድ በም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን?


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በላኝ፤ ከፋ​ፈ​ለ​ኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደ​ረ​ገኝ፤ እንደ ዘን​ዶም ዋጠኝ፤ ከሚ​ጣ​ፍ​ጠ​ውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።


ሴዴ​ቅ​ያስ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የል​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች።


ቤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ዕ​ቆ​ብን መል​ካም ነገር ሁሉ አሰ​ጠመ፤ አል​ራ​ራ​ምም፤ በመ​ዓቱ የይ​ሁ​ዳን ሴት ልጅ አን​ባ​ዎች አፈ​ረሰ፤ ወደ ምድ​ርም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቷ​ንና ግዛ​ቷ​ንም አረ​ከሰ።


ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ። አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ። በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን አበዛ።


የተ​ነ​ሡ​ብ​ኝን ሰዎች ከን​ፈ​ሮች ቀኑ​ንም ሁሉ ያሰ​ቡ​ብ​ኝን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሰማህ።


ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


ሰላም ሳይ​ኖር፦ ሰላም እያሉ ሕዝ​ቤን አታ​ል​ለ​ዋ​ልና፤ አን​ዱም ሰው ቅጥር ሲሠራ እነ​ርሱ ያለ​ገ​ለባ ይመ​ር​ጉ​ታል፤ ይወ​ድ​ቃ​ልም፤


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤


ምድ​ርም ከእ​ነ​ርሱ መጥ​ፋት የተ​ነሣ ባዶ ትቀ​ራ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ሳይ​ኖሩ በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ዕረ​ፍት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ፍር​ዴ​ንም ስለ ናቁ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ሥር​ዐ​ቴን ስለ ተጸ​የ​ፈች የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ቅጣት ይሸ​ከ​ማሉ።


በች​ግ​ራ​ቸ​ውም ቀን በሕ​ዝቤ በር ትገባ ዘንድ፥ በጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ቀን ጉባ​ኤ​ያ​ቸ​ውን ትመ​ለ​ከት ዘንድ፥ በእ​ል​ቂ​ታ​ቸ​ውም ቀን በሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ላይ አደጋ ትጥል ዘንድ አይ​ገ​ባ​ህም ነበር።


ይሰ​ድ​ቡ​ናል፥ እን​ማ​ል​ዳ​ቸ​ዋ​ለን፤ በዓ​ለም እንደ ጊጤ ሆን፤ በሁ​ሉም ዘንድ የተ​ና​ቅን ሆን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ እነ​ርሱ በሚ​ወ​ስ​ድህ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሁሉ የደ​ነ​ገ​ጥህ፥ ለም​ሳ​ሌና ለተ​ረ​ትም ትሆ​ና​ለህ።


跟着我们:

广告


广告