Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በገ​ባ​ች​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስላ​ረ​ከ​ሳ​ች​ሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እና​ንተ የም​ሠራ አይ​ደ​ለ​ሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ይህን ሁሉ የማደርገው ስለ እናንተ ብዬ ሳይሆን፣ በየሄዳችሁባቸው አሕዛብ መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ የምሠራው ስለ እናንተ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው በመንግሥታት መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “እንግዲህ እነሆ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምልህን ሁሉ ንገራቸው፤ ከእንግዲህ ወዲህ የማደርግላችሁ ነገር በሄዳችሁበት ስፍራ ሁሉ ስላሰደባችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ እንጂ ስለ እናንተ ስለ እስራኤላውያን ብዬ አይደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በመጣችሁባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ የምሠራ አይደለሁም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:22
15 交叉引用  

ስለ እኔም፥ ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትም ይህ​ችን ከተማ እጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ ይህን ለአ​ንተ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ስሜ ተነ​ቅ​ፎ​አ​ልና፤ ክብ​ሬ​ንም ለሌላ አል​ሰ​ጥም።


ታላ​ቆ​ቹ​ንና ታና​ሾ​ቹን እኅ​ቶ​ች​ሽ​ንም በተ​ቀ​በ​ልሽ ጊዜ መን​ገ​ድ​ሽን ታስ​ቢ​ያ​ለሽ፤ ታፍ​ሪ​ማ​ለሽ፤ ለአ​ን​ቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ቃል ኪዳ​ንሽ ግን አይ​ደ​ለም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እንደ ክፉ መን​ገ​ዳ​ች​ሁና እንደ ርኩስ ሥራ​ችሁ ሳይ​ሆን ስለ ስሜ ስል በሠ​ራ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአሉ፥ ከግ​ብ​ጽም ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ በፊ​ታ​ቸው በተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ላ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ስሜ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ይህን የሠ​ራሁ ስለ እና​ንተ እን​ዳ​ይ​ደለ በእ​ና​ንተ ዘንድ የታ​ወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ሩና ተዋ​ረዱ።


“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሁን የያ​ዕ​ቆ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ እራ​ራ​ለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀ​ና​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ እና​ንተ የሰ​ቀ​ላ​ች​ሁ​ትን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታም መሢ​ሕም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በር​ግጥ ይወቁ።”


跟着我们:

广告


广告