ሕዝቅኤል 36:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ወደ ገቡባቸውም ወደ አሕዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድራቸው የወጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 በአሕዛብ መካከል በሄዱበት ሁሉ ቅዱስ ስሜን አረከሱ፤ ስለ እነርሱ፣ ‘እነዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ናቸው፤ ዳሩ ግን የርሱን ምድር ትተው እንዲሄዱ ተገደዱ’ ተብሏልና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ወደ ሄዱባቸውም ወደ ሕዝቦች በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድሩ የወጡ የጌታ ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 እነዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ እርሱ ከሰጣቸው ምድር ወጥተዋል” ብለው የተበታተኑባቸው አገሮች ሕዝቦች ስለሚናገሩ ሕዝቤ ቅዱስ ስሜን አሰድበዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ወደ መጡባቸውም ወደ አሕዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድሩ የወጡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ። 参见章节 |