Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ አላ​ሰ​ማ​ብ​ሽም፤ ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ውር​ደት አት​ሸ​ከ​ሚም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን አታ​ሰ​ና​ክ​ዪም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከእንግዲህ የሕዝቦችን ዘለፋ እንድትሰሙ አላደርግም፤ በሰዎችም ስድብ አትሠቃዩም፤ ከእንግዲህ ለሕዝባችሁ መሰናክል አትሆኑም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አላሰማብሽም፥ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ምድሪቱ ከእንግዲህ ወዲህ የሕዝቦች ማላገጫ አትሆንም፤ በንቀትም አይመለከቱአትም፤ ምድሪቱንም ዳግመኛ ልጅ አልባ የሚያደርጋት አይኖርም። እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አላሰማብሽም፥ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:15
21 交叉引用  

የመ​ዓት ቍጣ​ቸ​ውን በላ​ያ​ችን ባነሡ ጊዜ፥ ሕያ​ዋን ሳለን በዋ​ጡን ነበር ብዬ በተ​ጠ​ራ​ጠ​ርሁ ነበር፥


አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።


የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽም ልጆች እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የና​ቁ​ሽም ሁሉ ወደ እግ​ርሽ ጫማ ይሰ​ግ​ዳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብ​ለ​ሽም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።


ፈረስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ በቀ​ላይ ውስጥ አሳ​ለ​ፋ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም አል​ደ​ከ​ሙም።


እኔም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም ደስ ይለ​ኛል፤ ከዚ​ያም ወዲያ የል​ቅሶ ድም​ፅና የዋ​ይታ ድምፅ በው​ስ​ጥዋ አይ​ሰ​ማም።


ሳይ​ጨ​ል​ም​ባ​ችሁ፥ ጨለ​ማም ባለ​ባ​ቸው ተራ​ሮች እግ​ሮ​ቻ​ችሁ ሳይ​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ስጡ፤ በዚ​ያም የሞት ጥላ አለና በጨ​ለ​ማ​ውም ውስጥ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ልና ብር​ሃ​ንን ተስፋ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።


ሕዝቤ ግን ረስ​ተ​ው​ኛል፤ ለከ​ንቱ ነገ​ርም አጥ​ነ​ዋል፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማ​ማ​ውና ወደ ሰን​ከ​ል​ካ​ላው መን​ገድ ለመ​ሄድ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ተሰ​ና​ከሉ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሞን ልጆ​ችና ስለ ስድ​ባ​ቸው እን​ዲህ ይላል ብለህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመ​ግ​ደል ተመ​ዝ​ዞ​አል፤ ጨር​ሶም ያርድ ዘንድ ተሰ​ን​ግ​ሎ​አል በል።


ባፈ​ሰ​ስ​ሽው ደም በድ​ለ​ሻል፤ ባደ​ረ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ጣዖ​ታት ረክ​ሰ​ሻል፤ ቀን​ሽ​ንም አቀ​ረ​ብሽ፤ ዘመ​ን​ሽ​ንም አሳ​ጠ​ርሽ፤ ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ መሰ​ደ​ቢያ፥ ለሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ መሳ​ለ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ሁሽ።


የሰ​ላ​ምን ተክል አቆ​ም​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከራብ የተ​ነሣ በም​ድር አያ​ል​ቁም፤ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ሸ​ከ​ሙም።


ስለ​ዚህ ዳግ​መኛ ሰው በላ​ተኛ አት​ሆ​ኝም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጊም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ስለ​ዚህ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድር ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችም እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ ስለ ተሸ​ከ​ማ​ችሁ በቅ​ን​አ​ቴና በመ​ዓቴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ በአሉ አሕ​ዛብ ላይ እኔ እጄን አነ​ሣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ይሸ​ከ​ማሉ።


በዚ​ያም ቀን ጎግ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅ​ሠ​ፍቴ በመ​ዓቴ ይመ​ጣል ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ እህ​ል​ንና ወይ​ንን፥ ዘይ​ት​ንም እሰ​ድ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በእ​ርሱ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል መሰ​ደ​ቢያ አላ​ደ​ር​ጋ​ች​ሁም።


በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፥ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ።


እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥ ጠላትሽንም ጥሎአል፣ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም።


跟着我们:

广告


广告