Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 35:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ህም ሰው የማ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህ መኖሪያ አይሆኑም። ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለዘለዓለም ባድማ አደርግሃለሁ፥ ከተሞችህም ሰው አይኖርባቸውም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ ለዘለዓለሙ ምድራችሁን ባድማ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም በከተሞቻችሁ የሚኖር አይገኝም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለዘላለምም ባድማ አደርግሃለሁ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 35:9
16 交叉引用  

ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰ​ደ​ቢ​ያና መረ​ገ​ሚ​ያም እን​ድ​ት​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ይሆ​ናሉ።


አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ እን​ድ​ት​ሆን ታጠ​ፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተና​ግ​ረ​ሃል በል።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እጄን በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ባድ​ማም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ከቴ​ማ​ንና ከድ​ዳ​ንም ያመ​ለጡ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።


“ኤዶ​ም​ያ​ስና ነገ​ሥ​ታቷ፥ አለ​ቆ​ች​ዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰ​ይፍ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር


ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም አፈ​ራ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ባድማ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።


ሰው​ንና እን​ስ​ሳ​ው​ንም አበ​ዛ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ያፈ​ሩ​ማል፤ እንደ ጥን​ታ​ች​ሁም ሰዎ​ችን አኖ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቀድ​ሞም እንደ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ መል​ካም አደ​ር​ግ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ጅማ​ት​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሥጋ​ንም አወ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ቍር​በ​ትን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ትን​ፋ​ሽ​ንም አገ​ባ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሁሉ ምድ​ሪ​ቱን ከዴ​ብ​ላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድ​ማና በረሃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ሙታ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራ​ል​ሽም፤ እኔም ይቅር አል​ል​ሽም፤ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ሽም በመ​ካ​ከ​ልሽ ነው፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም፤ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ርኵ​ሰ​ት​ሽም በመ​ካ​ከ​ልሽ ነው፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ቀ​ሥፍ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


“በወ​ን​ድ​ምህ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ስለ ተደ​ረገ ኀጢ​አ​ትና ግድያ ኀፍ​ረት ይከ​ድ​ን​ሃል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ትጠ​ፋ​ለህ።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፥ የሳማ ስፍራና የጨው ጕድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፣ የሕዝቤም ቅሬታ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።


跟着我们:

广告


广告