Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 35:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የዘ​ለ​ዓ​ለም ጠላት ሁነ​ሃ​ልና፥ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ በኀ​ይ​ለ​ኛ​ይቱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በሰ​ይፍ እጅ ጥለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘እስራኤላውያን ቅጣታቸው እጅግ መራራ ከሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ፍዳቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ፣ የጥንቱን ቂም ቋጥረህ ለሰይፍ ስለ ዳረግሃቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የዘለዓለም ጥል ስላለህ በመጨረሻው የፍርዳቸው ጊዜ፥ በመከራቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ ‘ለብዙ ጊዜ ከቈየው ጥላቻችሁ የተነሣ በኃጢአቱ ምክንያት በደረሰበት የመጨረሻ ቅጣትና በመከራው ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ለሰይፍ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የዘላለም ጥል ስላለህ በመከራቸውም ጊዜ በኋለኛይቱ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 35:5
15 交叉引用  

በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል


ጻድቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፥ በእ​ር​ሱም ይታ​መ​ናል፤ ልባ​ቸ​ውም የቀና ሁሉ ይከ​ብ​ራሉ።


ስለ​ዚህ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለራብ ስጥ፤ ለሰ​ይ​ፍም እጅ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ላድ መካ​ንና መበ​ለ​ቶች ይሁኑ፤ ወን​ዶ​ቻ​ቸ​ውም በሞት ይጥፉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በጦ​ር​ነት ጊዜ በሰ​ይፍ ይመቱ።


አን​ተም ቀን​ህና የኀ​ጢ​አ​ትህ ቀጠሮ ጊዜ የደ​ረ​ሰ​ብህ፥ ርኩስ ኀጢ​አ​ተኛ የእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ሆይ!


በተ​ገ​ደ​ሉት ኀጢ​አ​ተ​ኞች አን​ገት ላይ ያኖ​ሩህ ዘንድ ከንቱ ራእ​ይን ሲያ​ዩ​ልህ፥ በሐ​ሰት ምዋ​ር​ትም ሲና​ገ​ሩ​ልህ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ ቀና​ቸው ደረሰ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ኤዶ​ም​ያስ በይ​ሁዳ ቤት ላይ በቀል አድ​ር​ጎ​አ​ልና፥ ቂምም ይዞ​አ​ልና፥ በቀ​ል​ንም ተበ​ቅ​ሎ​አ​ልና፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቀ​ልን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ በቀ​ላ​ቸ​ው​ንም አጽ​ን​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጠፉ ዘንድ ነፍ​ሳ​ቸው ደስ ይላ​ታ​ልና፤


አን​ተም፦ ፈር​ሰ​ዋል፤ መብ​ልም ሆነው ለእኛ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል ብለህ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ስድብ ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰማ​ሁት ታው​ቃ​ለህ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያሳ​ድ​ዱ​አ​ትና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አት ዘንድ በል​ባ​ቸው ሁሉ ደስ​ታና በነ​ፍ​ሳ​ቸው ንቀት ምድ​ሬን ርስት አድ​ር​ገው ለራ​ሳ​ቸው በሰጡ በቀ​ሩት አሕ​ዛ​ብና በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ላይ በቅ​ን​አቴ እሳት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድር እን​ዲህ ይላል፦ ፍጻሜ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ መጣ፤ በም​ድ​ሪቱ በአ​ራ​ቱም ማዕ​ዘን ፍጻሜ መጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ይዘ​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ምርኮ ማር​ከ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


跟着我们:

广告


广告