Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 34:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረ​ኞች ስለ​ሌሉ፥ እረ​ኞ​ችም በጎ​ችን ስላ​ል​ፈ​ለጉ፥ እረ​ኞ​ችም ራሳ​ቸ​ውን እንጂ በጎ​ችን ስላ​ላ​ሰ​ማሩ፥ በጎች ንጥ​ቂያ ሆነ​ዋ​ልና፥ በጎ​ችም ለዱር አራ​ዊት ሁሉ መብል ሆነ​ዋ​ልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በሕያውነቴ እምላለሁ፣ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እረኞቼ መንጋዬን ስላልፈለጉ፣ ከመንጋዬም ይልቅ ራሳቸውን ስለ ተንከባከቡ፣ መንጋዬ እረኛ ዐጥቶ ለንጥቂያ ተዳርጓል፤ ለአራዊትም ሁሉ መብል ሆኗል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔም ሕያው ነኝና እረኛ ስለ ሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ እረኞቼ በጎቼን በመመገብና በመጠበቅ ፈንታ ራሳቸውን ብቻ ስለሚመግቡና የጠፉትን በጎቼን የሚፈልግና የሚጠብቅ እረኛ ስለሌላቸው የአውሬ ሲሳይ ሆነው ተበልተዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔም ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 34:8
14 交叉引用  

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በእ​ረ​ኞች ላይ ነኝ፤ በጎ​ች​ንም ከእ​ጃ​ቸው እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በጎ​ች​ንም ከማ​ሰ​ማ​ራት አስ​ተ​ዋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ እረ​ኞች በጎ​ችን አያ​ሰ​ማ​ሩም፤ በጎ​ች​ንም ከአ​ፋ​ቸው አድ​ና​ለሁ፤ መብ​ልም አይ​ሆ​ኑ​ላ​ቸ​ውም።


የቀ​ረ​ውን ማሰ​ማ​ር​ያ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ የረ​ገ​ጣ​ች​ሁት፥ የተ​ሰ​ማ​ራ​ች​ሁ​በት መል​ካሙ መሰ​ማ​ርያ ባይ​በ​ቃ​ችሁ ነውን? የቀ​ረ​ው​ንስ ውኃ በእ​ግ​ራ​ችሁ ያደ​ፈ​ረ​ሳ​ች​ሁት፥ ጥሩ​ውን ውኃ መጠ​ጣ​ታ​ችሁ ባይ​በ​ቃ​ችሁ ነውን?


እና​ን​ተም በጎች፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


“ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤


ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ስለ​ዚህ፥ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ራ​ሮ​ችና ለኮ​ረ​ብ​ቶች፥ ለፈ​ሳ​ሾ​ችና ለሸ​ለ​ቆ​ዎች፥ ለም​ድረ በዳ​ዎች፥ ባዶ ለሆ​ኑ​ትና ለፈ​ረ​ሱት፥ በዙ​ሪያ ላሉት ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ምር​ኮና መሣ​ለ​ቂያ ለሆ​ኑት ከተ​ሞች እን​ዲህ ይላል፦


ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፣ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፣ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።


ከእኔ በኋላ ለመ​ን​ጋ​ዪቱ የማ​ይ​ራሩ ነጣ​ቂ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች እን​ደ​ሚ​መጡ እኔ አው​ቃ​ለሁ።


ወር​ቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብ​ስም ቢሆን ከእ​ና​ንተ ከአ​ንዱ ስንኳ አል​ተ​መ​ኘ​ሁም።


እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል።


የዐመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥


跟着我们:

广告


广告