Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 34:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በጎች በተ​ራ​ሮች ሁሉና በረ​ዘሙ ኮረ​ብ​ቶች ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ በጎ​ችም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነ​ዋል፤ የሚ​ፈ​ል​ግም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በጎቼ በየተራራው ሁሉና በየኰረብታው ላይ ተንከራተቱ። በምድር ሁሉ ተበተኑ፤ የፈለጋቸውም፤ የፈቀዳቸውም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም የለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህም በጎቼ በከፍተኞች ኰረብቶችና ተራራዎች ተንከራተቱ፤ በምድርም ገጽ ተበተኑ፤ የሚጠብቃቸውና ፈልጎ የሚያገኛቸውም የለም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፥ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 34:6
15 交叉引用  

ሰው​ነቴ በላዬ አለ​ቀ​ች​ብኝ፥ ልቤም በው​ስጤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።


ከወ​ለ​ድ​ሻ​ቸው ልጆ​ችሽ ሁሉ የሚ​ያ​ረ​ጋ​ጋሽ አጣሽ፤ ከአ​ሳ​ደ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ልጆ​ችሽ ሁሉ እጁን ሰጥቶ የሚ​ያ​ነ​ሣሽ የለም።


እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።


ሳይ​ጨ​ል​ም​ባ​ችሁ፥ ጨለ​ማም ባለ​ባ​ቸው ተራ​ሮች እግ​ሮ​ቻ​ችሁ ሳይ​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ስጡ፤ በዚ​ያም የሞት ጥላ አለና በጨ​ለ​ማ​ውም ውስጥ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ልና ብር​ሃ​ንን ተስፋ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።


“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነ​ዋል፤ እረ​ኞ​ቻ​ቸው አሳ​ቱ​አ​ቸው፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ የተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ከተ​ራራ ወደ ኮረ​ብታ ዐለፉ፤ በረ​ታ​ቸ​ው​ንም ረሱ።


“ስለ​ዚህ እረ​ኞች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤


ከእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሸሹ ይድ​ናሉ፤ መብ​ረ​ርን እን​ደ​ሚ​ማር ርግ​ብም በተ​ራራ ላይ ይሆ​ናሉ፤ እኔም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


ከእኔ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና ወዮ​ላ​ቸው! እኔ​ንም ስለ በደሉ ደን​ግ​ጠ​ዋል! እኔ ታደ​ግ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በሐ​ሰት ተና​ገ​ሩ​ብኝ።


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ።


እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።


跟着我们:

广告


广告