Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 34:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወተ​ቱን ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ጠጕ​ሩ​ንም ትለ​ብ​ሳ​ላ​ችሁ፤ የወ​ፈ​ሩ​ትን ታር​ዳ​ላ​ችሁ፤ በጎ​ቹን ግን አታ​ሰ​ማ​ሩም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ጮማውን ትበላላችሁ፤ ከጠጕሩ የተሠራውን ሱፍ ትለብሳላችሁ፤ የሰባውን ዐረዳችሁ፤ ነገር ግን መንጋውን አትንከባከቡትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጮማውን ትበላላችሁ ሱፉንም ትለብሳላችሁ፥ የሰቡትን ታርዳላችሁ፤ መንጋውን ግን አትጠብቁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወተቱን ትጠጣላችሁ፤ ከጠጒራቸው የተሠራውንም ሱፍ ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም በግ ዐርዳችሁ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን በጎችን በማሰማራት አትጠብቁም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ፥ የወፈሩትን ታርዳላችሁ፥ በጎቹን ግን አታሰማሩም።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 34:3
18 交叉引用  

ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


እና​ንተ የሰ​ዶም አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እና​ንተ የገ​ሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አድ​ምጡ።


እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


ልጆ​ቻ​ች​ሁን በከ​ንቱ ቀሥ​ፌ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተግ​ሣ​ጼን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁም፤ ሰይ​ፋ​ችሁ እን​ደ​ሚ​ሰ​ብር አን​በሳ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በል​ቶ​አል፤ በዚ​ህም አል​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።


እነሆ ዐይ​ን​ህና ልብህ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ለቅ​ሚያ፥ ንጹሕ ደም​ንም ለማ​ፍ​ሰስ፥ ግድ​ያ​ንና ግፍ​ንም ለመ​ሥ​ራት ብቻ ነው።”


ሜም። የጻ​ድ​ቃ​ንን ደም በው​ስ​ጥዋ ስላ​ፈ​ሰሱ፥ ስለ ነቢ​ያቷ ኀጢ​አ​ትና ስለ ካህ​ናቷ በደል ነው።


ከግ​ል​ገ​ሎ​ች​ዋም አን​ዱን አወ​ጣች፤ እር​ሱም ደቦል አን​በሳ ሆነ፤ ንጥ​ቂ​ያ​ንም ተማረ፤ ሰዎ​ች​ንም ነጥቆ በላ።


እር​ሱም በአ​ን​በ​ሶች መካ​ከል አደገ፤ ደቦል አን​በ​ሳም ሆነ፤ ንጥ​ቂ​ያም ተማረ፤ ሰዎ​ች​ንም ነጥቆ በላ።


ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


እነሆ፥ በአገሩ ውስጥ እረኛ አስነሣለሁ፣ እርሱም የጠፋውን አያስብም፥ የባዘነውን አይፈልግም፥ የተሰበረውን አይጠግንም፣ የዳነውንም አይቀልብም፥ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፥ ሰኰናውንም ይቀለጣጥማል።


የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ ራሳቸውንም እንደ በደለኞች አድርገው አይቈጥሩም፣ የሸጡአቸውም፦ ባለ ጠጋ ሆነዋልና እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ፣ እረኞቻቸውም አይራሩላቸውም።


跟着我们:

广告


广告