Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ከመ​ን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብታ​ስ​ጠ​ነ​ቅ​ቀው፥ እር​ሱም ከመ​ን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነገር ግን ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው ከመንገዱ ባይመለስ፣ እርሱ ስለ ኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ራስህን አድነሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ሰው ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኃጢአተኛውን ሰው ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ካስጠነቀቅኸው በኋላ፥ ከክፉ ሥራው ሳይመለስ በኃጢአቱ ጸንቶ ቢሞት ግን፥ አንተ ራስህን ከኀላፊነት ነጻ ታደርጋለህ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:9
24 交叉引用  

የቅኖች ትምህርት በሚያልፉ ሰዎች ትታወቃለች። ተግሣጽን የሚጠሉ ግን በውርደት ይሞታሉ።


ነገር ግን አንተ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብት​ገ​ሥ​ጸው እር​ሱም ከኀ​ጢ​አ​ቱና ከክፉ መን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።


ነገር ግን ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሠራ ጻድ​ቁን ብት​ገ​ሥ​ጸው፥ እር​ሱም ኀጢ​አት ባይ​ሠራ፥ ጻድቅ ነውና በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ አን​ተም ነፍ​ስ​ህን አድ​ነ​ሃል።”


እር​ሱም በም​ድር ላይ የመ​ጣ​ውን ጦር በአየ ጊዜ መለ​ከ​ትን ቢነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ቢያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፤


የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ የሚ​ሰማ ሰው ባይ​ጠ​ነ​ቀቅ፥ ጦር መጥቶ ቢወ​ስ​ደው፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል።


ጕበ​ኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለ​ከ​ቱ​ንም ባይ​ነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ባያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእ​ነ​ርሱ ቢወ​ስድ፥ እርሱ በኀ​ጢ​አቱ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ ደሙን ግን ከጕ​በ​ኛው እጅ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


የጌ​ታ​ውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማ​ይ​ሠ​ራና የማ​ያ​ዘ​ጋጅ የዚያ አገ​ል​ጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው።


እነሆ፥ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ እን​ዳ​ል​ኋ​ችሁ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ባታ​ምኑ በኀ​ጢ​ኣ​ት​ችሁ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።”


እን​ግ​ዲህ እን​ዲህ የሚ​ለው የነ​ቢ​ያት ቃል እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ባ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


‘እነሆ፥ እና​ንተ የም​ታ​ቃ​ልሉ፥ እዩ፤ ተደ​ነ​ቁም፤ ያለ​ዚያ ግን ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ማንም ቢነ​ግ​ራ​ችሁ የማ​ታ​ም​ኑ​ትን ሥራ እኔ በዘ​መ​ና​ችሁ እሠ​ራ​ለ​ሁና።’ ”


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።


እኔ ከሁ​ላ​ች​ሁም ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ እነሆ ዛሬ በዚች ሌሊት እመ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ?


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


跟着我们:

广告


广告