ሕዝቅኤል 33:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ጕበኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለከቱንም ባይነፋ፥ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኀጢአቱ ተወስዶአል፤ ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ነገር ግን ጕበኛ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ፣ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ሳይነፋ ቢቀርና ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት ሰይፍ ቢያጠፋ፣ ያ ሰው ስለ ኀጢአቱ ይወሰዳል፤ ጕበኛውን ግን ስለ ሰውየው ደም ተጠያቂ አደርገዋለሁ።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ዘበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ አይቶ መለከቱን ባይነፋ፥ ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፥ ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኃጢአቱ ተወስዶአል ደሙን ግን ከዘበኛው እጅ እፈልጋለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ነገር ግን ጠባቂው ጠላት ሲመጣ እያየ ከአደጋ ማስጠንቀቂያውን ድምፅ ሳያሰማ ቢቀር፥ ጠላት መጥቶ ከእነዚያ መካከል አንዱን ቢገድል ያ ሰው የሞተው በኀጢአቱ ነው፤ እኔ ግን ስለ እርሱ ለደሙ ኀላፊ አድርጌ የምጠይቀው ጠባቂውን ነው።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ጕበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ ቢያይ መለከቱንም ባይነፋ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኃጢአቱ ተወስዶአል ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ። 参见章节 |