Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔም ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን ቢያ​ደ​ርግ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንዲሁም ክፉውን ሰው፣ ‘በርግጥ ትሞታለህ’ ብለው፣ እርሱም ከኀጢአቱ ተመልሶ ቀናውንና ትክክለኛውን ነገር ቢያደርግ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እኔም ኃጢአተኛውን ሰው፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንድን ክፉ ሰው በእርግጥ እንደሚሞት ባስታውቀውና እርሱ ግን ኃጢአት መሥራቱን ትቶ ሕጋዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔም ኃጢአተኛውን፦ በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:14
17 交叉引用  

እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


እስ​ራ​ኤል ወደ እኔ ቢመ​ለስ ይመ​ለስ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ርኵ​ሰ​ቱ​ንም ከአፉ ቢያ​ስ​ወ​ግድ፤ ከፊ​ቴም የተ​ነሣ ቢፈራ፥


እኔም ያል​መ​ለ​ስ​ሁ​ትን የጻ​ድ​ቁን ልብ ወደ ዐመፃ መል​ሳ​ች​ኋ​ልና፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መን​ገድ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውን እጅ አበ​ር​ት​ታ​ች​ኋ​ልና፤


“ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጋት ኀጢ​አት ሁሉ ቢመ​ለስ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ቢጠ​ብቅ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከሠ​ራው ኀጢ​አት ቢመ​ለስ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ነፍ​ሱን ይጠ​ብ​ቃል።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ቢያ​ደ​ርግ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ር​በ​ታል።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ ኀጢ​አ​ተኛ ሆይ! በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ከክፉ መን​ገዱ ታስ​ጠ​ነ​ቅቅ ዘንድ ባት​ና​ገር፥ ያ ኀጢ​አ​ተኛ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ ደሙን ግን ከእ​ጅህ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።


አሦር አያ​ድ​ነ​ንም፤ በፈ​ረ​ስም ላይ አን​ቀ​መ​ጥም፤ ድሃ​አ​ደ​ጉም በአ​ንተ ዘንድ ይቅ​ር​ታን ያገ​ኛ​ልና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የእ​ጆ​ቻ​ች​ንን ሥራ አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ አን​ላ​ቸ​ውም።”


ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?


ነገር ግን ሄዳችሁ ‘ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም፤’ ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኀጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤” አላቸው።


እን​ግ​ዲህ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ይሰ​ረ​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ንስሓ ግቡ፥ ተመ​ለ​ሱም።


跟着我们:

广告


广告