Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት፦ እና​ንተ፦ በደ​ላ​ች​ንና ኀጢ​አ​ታ​ችን በላ​ያ​ችን አሉ፤ እኛም ሰል​ስ​ለ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ዴ​ትስ በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን? ብላ​ችሁ ተና​ግ​ራ​ች​ኋል በላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘እንዲህ ትላላችሁ፤ “በደላችንና ኀጢአታችን ከብዶናል፤ ከዚህም የተነሣ ልንጠፋ ነው፤ ታዲያ እንዴት መኖር እንችላለን?” ’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ቤት፦ እናንተ፦ በደላችንና ኃጢአታችን በላያችን አሉ በእነርሱም እየመነመንን ነው፤ እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችሁ ተናግራችኋል በላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ “እናንተ በደላችንና ኃጢአታችን ከብደውናል፤ በእነርሱም ምክንያት እየመነመንን ነው፥ ታዲያ እንዴት መኖር እንችላለን ብላችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ቤት፦ እናንተ፦ በደላችንና ኃጢአታችን በላያችን አሉ እኛም ሰልስለንባቸዋል፥ እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችሁ ተናግራችኋል በላቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:10
12 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ በይ​ሁዳ ንጉሥ ፊት በተ​ነ​በ​በው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፥


አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አም​ል​ጠን ቀር​ተ​ናል፤ እነሆ በፊ​ትህ በበ​ደ​ላ​ችን አለን፤ ስለ​ዚህ በፊ​ትህ ሊቆም የሚ​ችል የለም።”


ጽዮን ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ኛል፤ ጌታም ረስ​ቶ​ኛል” አለች።


ልጆ​ችሽ ዝለ​ዋል፤ እንደ ጠወ​ለገ ቅጠ​ልም በየ​መ​ን​ገዱ ዳር ወድ​ቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣና ተግ​ሣጽ ተሞ​ል​ተ​ዋል።


እግ​ር​ሽን ከሰ​ን​ከ​ል​ካላ መን​ገድ፥ ጕሮ​ሮ​ሽ​ንም ከውኃ ጥም ከል​ክዪ፤ እር​ስዋ ግን፥ “እጨ​ክ​ና​ለሁ፤ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ወድ​ጄ​አ​ለሁ” ብላ ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው።


“እና​ንተ ግን፦ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት ስለ ምን አይ​ሸ​ከ​ምም? ትላ​ላ​ችሁ። ልጅ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን በአ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ በጠ​በ​ቀና በአ​ደ​ረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።


መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ች​ሁም በራ​ሳ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ይሆ​ናል፤ ዋይ አት​ሉም፤ አታ​ለ​ቅ​ሱ​ምም፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁም ትሰ​ለ​ስ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሁላ​ች​ሁም ጓደ​ኞ​ቻ​ች​ሁን ታጽ​ና​ና​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል።


ይህም እን​ጀ​ራ​ንና ውኃን እን​ዲ​ያጡ፥ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም እን​ዲ​ገ​ዳ​ደሉ፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እን​ዲ​ጠፉ ነው።


እኔም እን​ዲህ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ሀ​ትን፥ ክሳ​ት​ንም፥ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ዝዝ፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠፋ ትኩ​ሳት አወ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም በከ​ንቱ ትዘ​ራ​ላ​ችሁ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችሁ ይበ​ሉ​ታ​ልና።


ከእ​ና​ን​ተም ተለ​ይ​ተው የቀ​ሩት ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ይጠ​ፋሉ፤ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀጢ​አት ደግሞ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ይቀ​ል​ጣሉ።


跟着我们:

广告


广告