Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በተ​ገ​ደ​ሉት መካ​ከል ከብ​ዛቷ ሁሉ ጋር መኝ​ታን አድ​ር​ገ​ው​ላ​ታል፤ መቃ​ብ​ርዋ በዙ​ሪ​ያዋ ነው፤ ሁሉም ያል​ተ​ገ​ረ​ዙና በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደሉ ናቸው፤ በሕ​ያ​ዋ​ንም ምድር ያስ​ፈሩ ነበር፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር እፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል፤ በተ​ገ​ደ​ሉ​ትም መካ​ከል ተሰ​ጥ​ተ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በመቃብሯ ዙሪያ ካለው መላው ሰራዊቷ ጋራ፣ በታረዱት መካከል መኝታ ተዘጋጅቶላታል። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ ሽብራቸው በሕያዋን ምድር ስለ ተነዛ፣ ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋራ ዕፍረታቸውን ይሸከማሉ፤ በታረዱትም መካከል ይጋደማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በመቃብሯ ዙሪያ በተገደሉት መካከል ከብዛትዋ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፤ ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ነበር ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፥ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ለዔላም ወታደሮችና ብዛት ላለው ሕዝብዋ በሰይፍ በተገደሉት መካከል ማረፊያ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ መቃብሮቻቸውም በዙሪያው ነበሩ፤ ሁሉም በእግዚአብሔር ሳያምኑ በጦርነት የተገደሉ ናቸው፤ እነርሱም የሕያዋንን ዓለም ያሸብሩ የነበሩ በጦርነት የተገደሉ ናቸው፤ ኀፍረታቸውንም ተከናንበው ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር አብረው ይወርዳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በተገደሉት መካከል ከብዛትዋ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፥ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፥ በሕያዋንም ምድር ያስፈሩ ነበር ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፥ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:25
11 交叉引用  

የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሴቶች ልጆች ደስ እን​ዳ​ይ​ላ​ቸው፥ የቈ​ላ​ፋ​ንም ሴቶች ልጆች እልል እን​ዳ​ይሉ፥ በጌት ውስጥ አታ​ውሩ፤ በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናም አደ​ባ​ባይ የም​ስ​ራች አት​በሉ።


ሳኦ​ልም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “እነ​ዚህ ቈላ​ፋን መጥ​ተው እን​ዳ​ይ​ዘ​ብ​ቱ​ብኝ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግ​ሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበ​ርና እንቢ አለ። ሳኦ​ልም ሰይ​ፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።


አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ከም​ኞቴ የተ​ነሣ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች አት​ስ​ጠኝ፤ በላዬ ተማ​ከሩ፥ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ዩም አት​ተ​ወኝ።


በው​በት የም​ት​በ​ል​ጪው ማን ነው? ውረጂ ካል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትም ጋር ተኚ።


የኀ​ያ​ላን አለ​ቆች በሲ​ኦል ውስጥ ሆነው ከረ​ዳ​ቶቹ ጋር ይና​ገ​ሩ​ታል፤ በሰ​ይ​ፍም የተ​ገ​ደ​ሉት ያል​ተ​ገ​ረዙ ወር​ደው ተኝ​ተ​ዋል።


“ኤላ​ምም በዚያ አለች፤ ኀይ​ል​ዋም ሁሉ በመ​ቃ​ብ​ርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ሁሉ በሰ​ይፍ ወድ​ቀው ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ ሳይ​ገ​ረ​ዙም ወደ ታች​ኛው ምድር ወር​ደ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን አግ​ኝ​ተ​ዋል።


እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ከአ​ሉት ሁሉ በል​ቡና በሥ​ጋው ያል​ተ​ገ​ረዘ የባ​ዕድ ልጅ እን​ግዳ ሁሉ ወደ መቅ​ደሴ አይ​ግባ።


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


እነሆ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሓ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤


跟着我们:

广告


广告