Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይኸ​ውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ የአ​ሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ያሞ​ሹ​ለ​ታል፤ ስለ ግብ​ፅና ስለ ኀይ​ልዋ ሁሉ ያሞ​ሹ​ለ​ታል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ስለ እርሷ የሚያወርዱት ሙሾ ይህ ነው፤ የሕዝቦች ሴት ልጆች ያዜሙታል፤ ስለ ግብጽና ስለ ብዙ ሰራዊቷ ሁሉ ሙሾ ያወርዳሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሚያወርዱት ሙሾ ይህ ነው፤ የአሕዛብ ቆነጃጅት፤ በግብጽና ብዛትዋ ሁሉ ላይ ሙሾን ያወርዳሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህ የሚያወርዱት ሙሾ ነው፤ የሀገሪቱ ሴቶች ሙሾ ያሰማሉ፤ ለግብጽና ብዛት ላለው ሕዝብዋ ያወርዱታል፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የሚያለቅሱበት ልቅሶ ይህ ነው፥ የአሕዛብ ቈነጃጅት ያለቅሱበታል፥ ስለ ግብጽና ስለ ብዛትዋ ሁሉ ያለቅሱበታል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:16
7 交叉引用  

ዳዊ​ትም ስለ ሳኦ​ልና ስለ ልጁ ዮና​ታን ይህን የኀ​ዘን ቅኔ ተቀኘ፤


ኤር​ም​ያ​ስም ለን​ጉሡ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ የል​ቅሶ ግጥም ገጠ​መ​ለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወን​ዶ​ችና ሴቶች መዘ​ም​ራን ሁሉ በል​ቅሶ ግጥ​ማ​ቸው ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ይና​ገሩ ነበር፤ ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በል​ቅሶ ግጥም ተጽ​ፎ​አል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​መጡ አል​ቃ​ሾች ሴቶ​ችን ጥሩ፤ ወደ ብል​ሃ​ተ​ኞች ሴቶ​ችም ላኩ፤ መጥ​ተ​ውም ይን​ገ​ሩ​አ​ችሁ፤


በአ​ን​ቺም ላይ ሙሾ ያሞ​ሻሉ፤ እን​ዲ​ህም ይሉ​ሻል፦ በባ​ሕር የተ​ቀ​መ​ጥሽ፥ በባ​ሕ​ርም ውስጥ የጸ​ናሽ፥ ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ብ​ሽም ጋር በዙ​ሪ​ያሽ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ያስ​ፈ​ራሽ፥ የከ​በ​ርሽ ከተማ ሆይ! እን​ዴት ጠፋሽ!


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እር​ስ​ዋ​ንና የብ​ር​ቱ​ዎ​ቹን አሕ​ዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ወደ ታች​ኛው ምድር ጣላ​ቸው።


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈር​ዖን ሙሾ አሙሽ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ የአ​ሕ​ዛ​ብን አን​በሳ መስ​ለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነ​ሃል፤ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም ወግ​ተ​ሃል፤ ውኃ​ው​ንም በእ​ግ​ርህ አደ​ፍ​ር​ሰ​ሃል፥ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም በተ​ረ​ከ​ዝህ ረግ​ጠ​ሃል።


跟着我们:

广告


广告