ሕዝቅኤል 32:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የግብፅንም ምድር ባድማና ውድማ በአደረግሁ ጊዜ፥ ምድርም በመላዋ በጠፋች ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ግብጽን ባድማ ሳደርጋት፣ ምድሪቱም ያላትን ሁሉ ያጣች ስትሆን፣ በዚያም የሚኖሩትን ሁሉ ስመታ፣ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የግብጽንም ምድር ወና እና ባድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ ሞላዋንም ያጣች ምድር ባደረግኋት ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በመታሁ ጊዜ፥ እኔ ጌታ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እኔ ግብጽን ወና እና ባድማ በማደርግበትና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ በማጠፋበት ጊዜ፥ አንተና ሕዝብህ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የግብጽንም ምድር ባድማና ውድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ ሞላዋንም ያጣች ምድር ባደረግኋት ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 参见章节 |